1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ባንክ ዘገባ ኢትዮጵያ ና ኤርትራ

ረቡዕ፣ ሰኔ 1 2003

ኢትዮጵያን ጨምሮ በእድገት ወደኃላ የቀሩ አገራት ዘላቂ የምጣኔ ሀብት መዋቅር እንዲዘረጉ ተጠየቁ ።

https://p.dw.com/p/RSVl
ምስል ullstein - Giribas

የዓለም ባንክ ዛሬ ባወጣው ዘገባ ሃገራቱ ዘላቂ እድገትን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል ። በዚሁ ዘገባ ከዓለም የምጣኔ ሀብት ቀውስ በኃላ ድሃ ሀገራት ከበለፀጉት በበለጠ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገባቸውም ተገልጿል ። ዘገባው ኢትዮጵያ ከአካባቢ አገራት እጅግ ፈጣን ና ጠንካራ የምጣኔ ሃብት ዕድገት ማሳየቷንም ጠቁሟል ። የኤርትራ ኢኮኖሚም እያንሰራራ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።

አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ