1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ንግድ የዶሃ ድርድርና ዕጣው

ረቡዕ፣ ጳጉሜን 2 2003

የዓለም ንግድ ድርጅት የዶሃ ድርድር ዙር ከተጀመረ ይሄው ዘንድሮ በቅርቡ በሕዳር ወር አሥረኛ ዓመቱን ሊይዝ ነው። ይሁን እንጂ ፍትሃዊ ንግድን በማስፈን የታዳጊውን ዓለም የኤኮኖሚ ዕድገት ወደፊት ለማራመድ የታለመው ሕልም እስካሁን ዕውን ሊሆን አልቻለም።

https://p.dw.com/p/RkNw
ዋና ሃላፊ ፓስካል ላሚይምስል AP

የዶሃው ድርድር ዙር ዛሬ በብዙዎች ዘንድ አይሙት እንጂ ሊሞት የሚያጣጥር ነገርን ያህል ሆኖ ነው የሚታየው። በኢንዱስትሪ ልማት በበለጸጉትና በተፋጠነ ዕድገት ላይ በሚገኙት፤ በተለይም ሕንድን፣ ቻይናንና ብራዚልን በመሳሰሉት መንግሥታት መካከል የተፈጠረው መሠረታዊ ቅራኔ ሊታረቅ ሳይችል እንደቀጠለ ነው። የበለጸጉት መንግሥታት በበኩላቸው ለገበሬዎቻቸው የሚሰጡትን የእርሻ ድጎማ በአግባብ ለመቀነስና ገበዮቻቸውን ለታዳጊዎቹ ለመክፈት ብዙም ፈቃደኛ ሣይሆኑ ቀጥለዋል። አዳጊዎቹ አገሮችም በፊናቸው ገበዮቻቸውን ለበለጸጉት አገሮች የኢንዱስትሪ ምርቶችና አገልግሎቶች ጨርሰው መክፈቱን ይፈሩታል። ይህ እንግዲህ መፍትሄ ያጣው ከባድ ቅራኔ ሲሆን የበለጸጉት መንግሥታት በዚህ መሃል ከተናጠል መንግሥታትና የአካባቢ ቡድኖች ጋር የሁለት ወገን የንግድ ውል የማስፈን መንገድ መምረጣቸው ደግሞ ጉዳዩን ይበልጥ ሳያከብደው አልቀረም። ታዲያ በዚህ ሁኔታ ድርድሩን በስኬት ከግብ ማድረስ የሚቻል ነገር ነወይ? በጉዳዩ በስኮትላንድ-ዳንዲ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ንግድ ምሑር የሆኑትን ባለሙያ ዶር/ዶክተር መላኩ ደስታን አነጋግረናል።

መሥፍን መኮንን

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ