1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም አቀፍ የባህል ቀን በአዲስ አበባ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 12 2011

 የኢትዮጵያ የቅርስ ባለአደራ ማህበር በፅህፈት ቤቱ ባዘጋጀው ስነ ስርዓት የዓለም አቀፍ የባህል ቀን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እና ዓውደ ርዕይ ለሁለት ተከታታይ ቀናት አዲስ አበባ ውስጥ ተከበረ።  

https://p.dw.com/p/3H9iK
Äthiopien | International Day for Culture
ሊቀ ካህናት አባይነህ አበበምስል DW/G.T.Hailegiorgis

የዓለም አቀፍ የባህል ቀን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እና ዓውደ ርዕይ ለሁለት ተከታታይ ቀናት አዲስ አበባ ውስጥ ተከበረ።  የኢትዮጵያ የቅርስ ባለአደራ ማህበር በፅህፈት ቤቱ ባዘጋጀው ስርዓት ላይ የማህበሩ ዓላማ እና ያከናወናቸውን ተግባራት ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ ሊቀ ካህናት አባይነህ አበበ «በአጼ ሚኒሊክ ዘመነ መንግሥት የተገነባው በለገሃር የሚገኘው የምድር ባቡር ጣቢያ በመልሶ ማልማት ምክንያት  ሊፈርስ ሲወሰንለት ከመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር  በቅርስነት እንዲጠበቅ ማህበራችን አድርጓል» ብለዋል። ይህንኑ ስነ ስርዓት ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታትሏል። ዝርዝሩን ከድምፅ ዘገባው ያገኛሉ።

 

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ልደት አበበ