1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ውድድር

ሰኞ፣ ሰኔ 23 2006

ብራዚል ውስጥ በመካሄድ ላይ ያለው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር በአጓጊነቱና በልብ ሰቃይነቱ ቀጥሏል ። 16 ቡድኖች ከተሰናበቱበት የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ፍፃሜ በኋላ የቀጠለው የጥሎ ማለፉ ግጥሚያ ባለፈው ቅዳሜ በአስተናጋጇ በብራዚል አሸናፊነት

https://p.dw.com/p/1CSsE
ምስል Getty Images

አንድ ተብሎ ዛሬ ሶስተኛው ቀን ግጥሚያ ላይ ደርሰናል ። እስካሁን ኮሎምቢያ ኔዘርላንድስና ኮስታሪካ ወደ ቀጣዩ ጨዋታ አልፈዋል ። የዛሬው ምሽት ውድድር በናይጀሪያና ፈረንሳይ እንዲሁም በጀርመንና በአልጀሪያ መካከል የሚካሄደው ነው።

የዛሬው ውድድር ፤ አፍሪቃውያን ትልቅ ግምት የሚሰጡት ግጥሚያ ነው ። በዚህ በጀርመን ሀገር እጅግ ሰፋ ያለ የመገናኛ ብዙኀን ሽፋን ሲያገኝ የሰነበተውና ዛሬም የተሰጠው ፣ ከናይጀሪያና ፈረንሳይ ግጥሚያ ይልቅ የጀርመንና የአልጀሪያ ውድድር ነው። ጠንካራ ግብ ጠባቂ ፣ ፈጣን የመኻል ሜዳ አከፋፋዮችና አጥቂዎች ያሉት የጀርመን ብሔራዊ ቡድን፤ ከጋና ጋር ካደረገው ግጥሚያ ወዲህ ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ፣ ዛሬ ነው ጥንካሬው የሚለካው። አልጀሪያውያን ፤ ከኳስ ፍቅር ችሎታና ድፍረት ጋር እንዴት ይሆን ዝግጅታቸው? በአካባቢያችን ፣ ማለትም በኮሎኝ ኑዋሪ የሆነውን የእግር ኳስ ባለሙያ፣ ክንፈ ወልደ መስቀልን ፣ አነጋግረናል ። ቀጣዩ የስፖርት ዝግጅት ዋነኛ ትኩረት በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ነው ያተኮረውን የዛሬውን የስፖርት ዝግጅት ያቀረበችልን የፓሪስዋ ዘጋቢአችን ሃይማኖት ጥሩነህ ናት።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ኂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ