የዓለም የምግብ ድርጅትና የአልሸባብ ዛቻ24 የካቲት 2002ረቡዕ፣ የካቲት 24 2002የዓለም የምግብ ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህፃር WFP ለሶማሊያ የሚሰጠውን ዕርዳታ እንዲያቆም አልሸባብ የተባለው የሶማሊያን መንግስት የሚወጋው ቡድን ቢያስጠነቅቅም የምግብ ተቋሙ በሶማሊያ ዕርዳታ መስጠቱን ለመቀጥል መወሰኑን አስታውቋል ።https://p.dw.com/p/MIpsምስል APማስታወቂያደቡባዊ እና ማዕከላዊ ሶማሊያን የሚቆጣጠረውና አልቃይዳ ከተባለ አሸባሪ ቡድን ጋር ቁርኝት አለው የሚባለው አልሸባብ ባለፈው ዓመት እንዳደረገው ሁሉ ከትናንት በስተያም የዓለም የምግብ ድርጅት ለሶማሊያ የምግብ ዕርዳታ እንዳያቀርብ ማገዱን አስታውቋል ። የሮሙ ወኪላችን ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ። ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ፣ ሂሩት መለሰ አርያም ተክሌ