1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የምግብ ፖሊሲ አመላካች ስብሰባ

ረቡዕ፣ ኅዳር 16 2002

ሚልዮኖችን መመገብ በሚል ርዕስ ረሀብን ለመታገል ያስችላሉ የተባሉ እና ባለፉት ሀምሳ ዓመታት በግብርናው ልማት ዘርፍ የታዩሀያ ምርጥ የዓለማችንን ተሞክሮ የያዘ ጥናት ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ይፋ ሆነ።

https://p.dw.com/p/Kg90
ምስል dpa

በዓለም የምግብ ጥናት ፖሊሲ ተቋም አስተባባሪነት የወጣው ጥናት ይፋ በሆነበት ጊዜ ፖሊሲ አጪዎች፡ የግብርና ባለሙያዎች፡ የአፍሪቃ ህብረት እና የተመድ ከፍተኛ ባለስልጣኖች፡ እንዲሁም፡ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆነ የዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች ተገኝተዋል። ጥናቱ ይፋ የሆነበትን ስብሰባ በክብር እንግድነት ተገኝተው የከፈቱት የኢትዮጵያ የግብርና እና የገጠር ሚንስትር አቶ ተፈራ ደርበው ናቸው።

ታደሰ እንግዳው/አርያም ተክሌ/ነጋሽ መሀመድ