1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የሴቶች የእግር ኳስ ጨዋታ 

ቅዳሜ፣ ሰኔ 1 2011

ወደ 14 ሽህ ተመልካቾች በተገኙበት ግጥምያ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዉን ተቆጣጥሮ ዘጠና ደቂቃዉን መጨረሱን ቦታዉ ላይ የምትገኘዉ የፈረንሳይዋ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ መረጃ አድርሳናለች።

https://p.dw.com/p/3K4kb
Frauenfussball-WM - Deutschland - China
ምስል Getty Images/M. Hitij

ፈረንሳይ ላይ በድምቀት በተጀመረዉ የ2019 የዓለም የሴቶች የእግር ኳስ ጨዋታ ግጥምያ ዛሬ በሁለተኛ ቀኑ እንደቀጠለ ነዉ። ቅዳሜ ከቀትር በኋላ ጀርመን ከቻይና ብሔራዊ ቡድን ጋር ተጋጥሞ የጀርመን የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የቻይና አቻዉን አንድ ለዜሮ ረቶአል። ወደ 14 ሽህ ተመልካቾች በተገኙበት ግጥምያ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዉን ተቆጣጥሮ ነዉ ዘጠና ደቂቃዉን የጨረሰዉ። ቅዳሜ ምሽት ላይ አፍሪቃን ወክላ በግጥምያዉ የምትሳተፈዉ ደቡብ አፍሪቃ ከስፔን ጋር ትጋጠማለች። ዘንድሮ አፍሪቃን ወክለዉ በሴቶች የዓለም እግርኳስ ግጥያ ላይ የሚሳተፉ ሃገሮች ደቡብ አፍሪቃ፣ ናይጄርያና ካሜሩን ናቸዉ። 

ሃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ