1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የጦር መሣሪያ ዝውውር

ማክሰኞ፣ የካቲት 15 2008

የስቶክሆልም ዓለም ዓቀፍ የሰላም ጥናት ተቋም በምህፃሩ «ሲፕሪ» ትናንት 50 ኛ ዓመቱን ሲያከብር ይፋ ባደረገው የጦር መሣሪያ ዝውውር መዘርዝር መሠረት በዚህ ጊዜ ውስጥ በጦር መሣሪያ ንግድ የመጀመሪያውን ደረጃ የምትይዘው ዩናይትድ ስቴትስ ለ96 ሃገራት የጦር መሣሪያዎችን ሸጣለች ።

https://p.dw.com/p/1I0er
Dan Smith Director SIPRI
ምስል DW/T. Meheretu

[No title]

በዓለማችን ከጎርጎሮሳዊው 2011 እስከ 2015 ከተሰራጨው የጦር መሣሪያ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የሚያመርቱና የሚያሰራጩ ዩናይትድ ስቴትስና ሩስያ መሆናቸው ተዘገበ ። የስቶክሆልም ዓለም ዓቀፍ የሰላም ጥናት ተቋም በምህፃሩ «ሲፕሪ» ትናንት 50 ኛ ዓመቱን ሲያከብር ይፋ ባደረገው የጦር መሣሪያ ዝውውር መዘርዝር መሠረት በዚህ ጊዜ ውስጥ በጦር መሣሪያ ንግድ የመጀመሪያውን ደረጃ የምትይዘው ዩናይትድ ስቴትስ ለ96 ሃገራት የጦር መሣሪያዎችን ሸጣለች ። ከዩናይትድ ስቴትስ የጦር መሣሪያ በመሸመት ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዘው ሳውዲ አረቢያ ስትሆን የተባበሩት አረብ ኤምሪቶችና ቱርክም ሁለተኛ ና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።የምዕራብ አውሮፓ ሃገራትም በጦር መሣሪያ ሽያጭ ከፍተኛ ቦታ ይይዛሉ ። የስቶክሆልሙ ወኪላችን SPRI 50 ኛ ዓመት በዓል አከባበር ተገኝቶዋል።

ቴድሮስ ምህረቱ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ