የዓለም የፋይናንስ ቀዉስና አፍሪቃ27 ጥር 2001ረቡዕ፣ ጥር 27 2001በዓለም የተከሰተዉ የፋይናንስ ቀዉስና የምጣኔ ሃብት ድቀት ለጋሽ አገራት ለአፍሪቃ የሚሰጡትን የልማት ርዳታ ሊያስተጓጉል እንደሚችል ስጋት አለ።https://p.dw.com/p/GnFV...የአፍሪቃ አገራት ምክክር ...ምስል picture-alliance/ dpaማስታወቂያአዲስ አበባ ዉስጥ ላለፉት ሶስት ቀናት ጉባኤ ተቀምጠዉ የነበሩት የአፍሪቃ መሪዎች ቀዉሱ አፍሪቃን ሳይጎዳ እንዲያልፍ ይበጃል ያሉትን ሃሳብ እያነሱ ተወያይተዋል። አፍሪቃ የፋይናንስ ቀዉሱ ቀጥተኛ ክንድ ባያርፍባትም ለጋሾች እጃቸዉ ሲያጥር የጀመረቻቸዉ የልማት መርሃግብሮችና ማኅበራዊ ተቋማት ከተፅዕኖ እንደማያመልጡ ተንታኞች እያሳሰቡ ነዉ።