1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ፕረስ ነፃነት ቀን

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 25 2004

የዓለም መገናኛ ብዙሃን ነጻነት ቀን የፕረስ ነፃነት ለማኅበረሰብ ለዉጥ ያግዛል በሚል መሪ ቃል ዛሬ በመላዉ ዓለም ታስቦ ዉሏል። የተመድ ዋና ፀሐፊ ባንጊሙን ዕለቱን አስመልክተዉ በድርጅቱ ዋና ጽህፈት ቤት በተካሄደ ዝግጅት ላይባስተላለፉት

https://p.dw.com/p/14pA2
ምስል dpa

መልክዕት ጋዜጠኞች ከስጋት ጋ ለመኖር መገደዳቸዉን አመልክተዉ፤ ባለፈዉ የአዉሮጳዉያን ዓመት 2011 ከ60 በላይ መገደላቸዉን፤ እጅግ በርካቶችም ከመንግስታት፤ ከኮርፖሬሽኖች እንዲሁም አቅም ካላቸዉ ግለሰቦች ወከባ፤ ማስፈራራትና ቅድመ ምርመራ እንደሚያጋጥማቸዉም ገልጸዋል። አዲስ አበባ ላይ ደግሞ በተለያዩ ተቋማት ዉስጥ የኢትዮጵያን የፕረስ ነጻነት ይዞታ የተመለከቱ ዉይይቶች እና ክርክሮች መካሄዳቸዉን ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ በላከዉ ዘገባ ያስረዳል።

ታደሰ እንግዳዉ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ