1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዙሪክ የዲያመንድ ሊግ

ዓርብ፣ ነሐሴ 19 2009

ትናንት ማምሻዉን የተጠናቀቀዉ የዙሪኩ ዲያመንድ ሊግ ዉድድር በተለይም የወንዶቹ የአምስት ሺህ ሜትር ርቀት አስገራሚ እና ድራማዊ አጨራረስ አስተናግዷል።

https://p.dw.com/p/2irZd
IAAF London Leichtathletik WM- Muktar Kedir Und Mo Farah
ምስል DW/H. Tiruneh

ከፍተኛ ፉክክር የታየበት ዉድድር ነበር፤

 እልህ አስጨራሽ እና የአንገት ላንገት ትንቅንቅ የታከለበት የአጨራረስ ዘዴ በታየበት በዚህ ዉድድር ብሪታኒያዊዉ ሞ ፋራህ ከዓለም ሻምፒዮናዉ ሙክታሪ ኢድሪስ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ የገጠመዉን ብርቱ ፉክክር ተቋቁሞ የትራክ ላይ የሩጫ ዘመኑን በድል ማጠናቀቅ ተሳክቶለታል። በዲያመንድ ሊጉም የፍጻሜ አሸናፊ መሆኑ የ50 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሲያደርገዉ ጠንካራ ተፎካካሪዎቹ ሙክታር እና ዮሚፍም ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመግባት ተሸላሚዎች ሆነዋል። በስፍራዉ ተገኝታ ዉድድሩን የተከታተለችዉ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝሩን ልካልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ