1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዚምባቡዌ ጥምር መንግስትና ኮሎኔል መንግስቱ

ሰኞ፣ ግንቦት 24 2001

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በዚምባቡዌ የስደት ህይወታቸዉን ከጀመሩ 18 ዓመታት ተቆጥረዋል።

https://p.dw.com/p/I1as
ምስል AP

ኮሎኔሉ በበርካታ ጉዳዮች ተጠያቂ መሆናቸዉን የሚጠቅሰዉ የኢትዮጵያ መንግስት ለፍርድ እንደሚያቀርባቸዉ መግለፁ አልቀረም። ዓመታት ዓመታትን ወልደዉ ያኔ ግንቦት 13ቀን 1983ዓ,ም በቀትር ከአገር የወጡት ኮሎኔል መንግስቱ ጓዳዊ ትብብር ካላቸዉ ከዚምባቡዌዉ ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ ሙሉ ከለላ ማግኘታቸዉ እንዳለ ሆኖ፤ አሁን አገሪቱ በጣምራ ፓርቲዎች አስተዳደር ስር ስትሆን ወደአገራቸዉ መላካቸዉ የማይቀርነዉ የሚሉ በርካቶች ቢሆኑም ፍንጭ የሚሰጡ ነገሮች ግን እስከአሁን አልታዩም።

ሸዋዬ ለገሠ/ ነጋሽ መሐመድ