1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዚምባቡዌ ፖለቲካዊ ቀዉስ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 16 2001

ዚምባቡዌ ለለየለየት ድቀት ቁል-ቁል እየጋላበች ነዉ።በአዉሮጳዉያኑ አምና የምግብ ርዳታ የሚያስፈልገዉ ሕዝብ ሁለት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ነበር።ዘንድሮ ወደ አምስት ሚሊዮን አሻቅቦል።

https://p.dw.com/p/G1oY
የሕዝብ «ማምላለሻ»ምስል picture-alliance/ dpa

የዚምባቡዌ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት ለመመስረት ያደረጉት ሥምምነት ገቢር ሥለሚሆንበት ሁኔታ ለመነጋገር ዛሬ ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ ተሰብስበዋል።እየተካረረ የመጣዉ የተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ዉዝግብ ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት ለመመስረት የተደረገዉን ሥምምነት ጨርሶ ያፈርሰዋል የሚል ሥጋት አሳድሯል።የፖለቲካዉ ዉዝግብ ያሳደረዉን ችግር ሲከታተል የሰነበተዉ የሽማግሌዎች መማክርት በበኩሉ ዚምባቡዌ ጨርሶ ከመዉደቅ አፋፋ ላይ እንደምትገኝ እያስጠነቀቀ ነዉ።ዛሬ የሚደረገዉ ስብሰባም ለችግሩ ሁነኛ መፍትሔ ማምጣቱ ብዙ አጠራጣሪ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ የዜና መልዕክቶችን አሰባስቧል።