1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዝርፊያ ወንጀል በእንጦጦ

ዓርብ፣ መጋቢት 6 2011

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ እንጦጦ ማርያም ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጫካ ዉስጥ ተደብቀዉ በሚንቀሳቀሱ ሰዎች ዝርፊያና ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑ ተገለፀ። ጥቃቱ  በአካባቢዉ ለጉብኝት በሚሄዱ የዉጭ ሀገር ሰዎች ላይ ሳይቀር ኢየተፈፀመ ነዉ ተብሏል።

https://p.dw.com/p/3F5hB
Äthiopien Straßen und Autos in Addis Abeba
ምስል DW/M. Sileshi

Robery in Addis Abeba-ENTOTO- - MP3-Stereo

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ እንጦጦ ማርያም ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጫካ ዉስጥ ተደብቀዉ በሚንቀሳቀሱ ሰዎች ዝርፊያና ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑ ተገለፀ። ጥቃቱ በአካባቢዉ ለጉብኝት በሚሄዱ የዉጭ ሀገር ሰዎች ላይ ሳይቀር ኢየተፈፀመ ነዉ ተብሏል። 
አንድ ስማቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉና ከአንድ ወር በፊት ከጀርመን ጎብኝዎችን ይዘዉ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸዉን የገለፁ ትዉልደ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ በስልክ ለDW እንደተናገሩት መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ/ም ከስዓት በኋላ በተለምዶ እንጦጦ ማርያም ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ዝርፊያና ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።በወቅቱ ይዘዉት የነበረዉ ገንዘብ፣ ካሜራና የዕጅ ስልክም እንደተወሰደባቸዉ  ተናግረዋል። በማስጎብኜት ስራ ላይ የተሰማሩ መሆናቸዉን የሚገልፁት እኝሁ ግለሰብ  ከሳምንት በፊት በአንዲት የዉጭ ሀገር ዜጋ ላይም ተመሳሳይ ጥቃት እንደተፈፀመ ከአካባቢዉ ሰዎች መስማታቸዉን ተናግረዋል። በወቅቱ አብረዋቸዉ የነበሩ የብሄራዊ አስጎብኝ ድርጅት አንድ ሃለፊም ጥቃት እንደደረሰባቸዉ አብራርተዋል።
ግለሰቡ ጉዳዩን በወቅቱ ለአካባቢዉ ፖሊስ ማሳወቃቸዉን ገልፀዉ ነገር ግን ተገቢ መልስ እንዳላገኙ አመልክተዋል።እናም የሚመለከታቸዉ አካላት የአካባቢዉን ፀጥታ ትኩረት ሰጥተዉ  እንዲጠብቁ  አሳስበዋል። ጉዳዩን በተመለከተ «DW» ጉዳዩ ይመለከተዋል የተባለዉን በአዲስ አበባ ከተማ የሽሮሜዳ የፖሊስ ፅ/ቤትን ያነጋገረ ሲሆን ስማቸዉን መግለፅ ያልፈለጉ የፅ/ቤቱ ፖሊስ «ወንጀልን ለመከላከል እየሰራን ነዉ» ከሚል ጥቅል መልስ ዉጭ ሌላማብራሪያ ሊሰጡንን አልፈቀዱም። በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኜት የአዲስ አበባ ፖሊስን ለማነጋገር ጥርት ብናደርግም ስብሰባ ላይ ነን በማለታቸዉ ምላሹን ልናካትት አልቻልንም። 

ሙሉ ቅንብሩን የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነዉ ያድምጡ።

ፀሀይ ጫኔ

እሸቴ በቀለ