1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የየመን ተፋላሚ ኃይላት ድርድር

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 5 2008

የተፋላሚ ኃይላት አቅም መዳክም፤ የሁቲ አማፂያንን የሚደበድቡት ሳዑዲአረቢያ መራሽ መንግሥታት ወጪ መናርና መሰላቸት ድርዱሩን እንደ ጥሩ አማራጭ እንዲታይ አድርጎታል።

https://p.dw.com/p/1HNj6
ምስል Reuters/M. al-Sayaghi

[No title]

የየመን ተፋላሚ ሐይላት ተወካዮች ዛሬ ስዊትዘርላንድ ዉስጥ አዲስ የሰላም ድርድር ጀምረዋል። በሳዑዲ አረቢያ የሚደገፈዉ የፕሬዝደንት አብድ ረቦ መንግሥት፤የሁቲ አማፂያን እና አማፂያኑን የሚረዱት ኃይላት ተወካዮች ለድርድር ሲቀመጡ ያሁኑ የመጀመሪያቸዉ አይደለም። ይሁንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አደራዳሪዎች እንደሚሉት ተፋላሚ ኃይላት ተኩስ ማቆምን ጨምሮ በበርካታ ቅድመ-ግዴታዎች ላይ ሥለተቀራረቡ ያሁኑ ድርድር አግባቢ ዉጤት ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል። የተፋላሚ ኃይላት አቅም መዳክም፤ የሁቲ አማፂያንን የሚደበድቡት ሳዑዲ አረቢያ መራሽ መንግሥታት ወጪ መናርና መሰላቸት ድርዱሩን እንደ ጥሩ አማራጭ እንዲታይ አድርጎታል። የሰነዓ ተባባሪ ዘጋቢያችን ግሩም ተክለ ሐይማኖት በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ግሩም ተክለ ሐይማኖት

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ