የየመን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ
ረቡዕ፣ የካቲት 21 2004ማስታወቂያ
የየመን ሕዝብ በአደባባይ ሠልፍ የተቃወማቸዉን የሐገሪቱን ፕሬዝዳት ዓሊ አብደላ ሳሌሕን እንዲተኩ የታጩትን የምክትል ፕሬዝዳት የአብድረቡሕ መንሱር ሐዲን ፕሬዝዳትነት ለማፅደቅ ዛሬ ድምፁን ሲሰጥ ዉሏል። የየመን ተቀናቃኝ ሐይላት በፋርስ ባሕረ-ሠላጤዉ አካባቢ ሐገራት ማሕበር ሸምጋይነት በደረሱበት ስምምነት መሠረት ዛሬ የፕሬዝዳትነት ሥልጣናቸዉ የሚፀድቅላቸዉ ሐዲ የመድብለ ፓርቲ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ሐገሪቱን ለሁለት አመት ይመራሉ።ከደቡብ የመን የሚወለዱትን የሐዲን ፕሬዝዳትነት ለደቡብ የመን ነፃነት የሚጠይቁት፥ የሺዓ ሁቱ አማፂያን እና ሕዝባዊን አመፅ ካስተባበሩት አንዳዶቹ ተቃዉመዉታል።የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።
ነብዩ ሲራክ
ነጋሽ መሃመድ
አርያም ተክሌ