1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩሊኽ የምርምር ማዕከልና ፣ በአውሮፓ እጅግ ግዙፉ ኮምፑዩተር፣

ረቡዕ፣ የካቲት 18 2001

በሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ ግሥጋሤ ያሳየው ሰው፣ በሥነ- ዕብን፣ በከርሠ-ምድር ፣ በተለይ በውቅያኖሶች ላይ፣ በውቅያኖስ ወለልና በወለሉ ሥር ፣ በቂ ምርምር እንዳልተካሄደ የታወቀ ነው።

https://p.dw.com/p/H176
ፕሮፌሰር ቶማስ ሊፐርት፣ የዩሊኽ የምርምር ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ምስል Forschungszentrum Jülich

በውቅያኖስ የሚገኙ እንስሳትና ዐራዊት ፣ የተለያዩ ነፍሳት በተለያዩ ደኖች የሚገኙ ዕጽዋትና ነፍሳት ፣ የምድር ነውጥ ፣ እሳተ-ገሞራዎች ፣ እነዚህና የመሳሰሉት የተሟላ ምርምር ተደርጎባቸዋል ማለት አይቻልም።

ለምርምር ሰፊ እገዛ የሚያደረጉ የሥነ- ቴክኒክ ውጤቶች መሆናቸው የማይታበል ሐቅ ነው። በመሆኑም ለዚህ የረጅም ጊዜ ግንዛቤ ያላት ጀርመን፣ በአውሮፓ እጅግ ግዙፉን የስሌት ኮምፑዩተር ኮሎኝ አቅራቢያ ዩሊኽ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ታዋቂ የምርምር ማዕከል እንደምትተክል አስታውቃለች።