1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኒሴፍ እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 26 2008

የሃይማኖት መሪዎች በእምነቶቻቸው መሠረት ፣በእናቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ሃይማኖታዊ ተቀባይነት የላቸውም ብለዋል ።

https://p.dw.com/p/1JaRb
UNICEF hat einen Vertrag mit ÄthiopienReligiöse Gemeinde unterschrieben
ምስል DW/Y.G.Egziabher

[No title]


የኢትዮጵያ ዋና ዋና የሃይማኖት ተቋማት በእናቶች እና በህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል እና የእናቶች እና ህፃናትን ጤና ለማስጠበቅ ከዩኒሴፍ ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን የመግባባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ ።ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የሃይማኖት መሪዎች በእምነቶቻቸው መሠረት ፣በእናቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ሃይማኖታዊ ተቀባይነት የላቸውም ብለዋል ።ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ