1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ

ረቡዕ፣ ሰኔ 15 2008

ዛሬ የተሰየመው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት በተማሪዎቹ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።

https://p.dw.com/p/1JBKQ
Symbolbild Justitia Justizia
ምስል Imago

[No title]

የካቲት 29፣ 2008 ዓም በአዲስ አበባው የአሜሪካን ኤምባሲ በር ላይ ያልተፈቀደ ሰልፍ በማካሄድ ደንብ ጥሳችኋል ተብለው በተከሰሱ 22 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዛሬ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው ብይን ለሌላ ጊዜ ተላለፈ ። ዛሬ የተሰየመው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት በተማሪዎቹ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። ችሎቱ ተከሳሾቹ ያቀረቡትን ንብረታቸውን የመረከብ አቤቱታም ተቀብሎ ትእዛዝ ሰጥቷል ። ስለ ዛሬው ችሎት የተማሪዎቹን ጠበቃ ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ