1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስ መርሕና አፍሪቃ

ረቡዕ፣ የካቲት 5 2006

አሜሪካዊዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር እንደሚሉት የደቡብ ሱዳን፣ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ እና የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክን ጦርነት፣ግጭትና ፖለቲካዊ ቀዉስን ለማስቆም ለማስቆም በሚደረገዉ ጥረት መንግሥታቸዉ ጉሉሕ አስተዋፅኦ እያደረገ ነዉ

https://p.dw.com/p/1B7XD
ምስል picture-alliance/AP Photo

ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪቃ ሠላም፥ ደሕንነትና ብልፅግናን ለማስፈን እየጣረች መሆንዋን የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ አስታወቁ።ኬሪ ትናንት ከአፍሪቃ ጉዳይ ምክትላቸዉ ጋር ሆነዉ በሠጡት መግለጫ እንዳሉት መንግሥታቸዉ በተለይ ጦርነት እና ግጭት የሚያብጣቸዉን ሐገራት ለመርዳት ልዩ ትኩረት ትሠጣለች።አሜሪካዊዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር እንደሚሉት የደቡብ ሱዳን፣ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ እና የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክን ጦርነት፣ግጭትና ፖለቲካዊ ቀዉስን ለማስቆም ለማስቆም በሚደረገዉ ጥረት መንግሥታቸዉ ጉሉሕ አስተዋፅኦ እያደረገ ነዉ።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ