1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫና ሁለቱ እጩዎች

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 25 2001

እንደ ዘር፣ ትዉልዳቸዉ ሁሉ በአስተሳሰብ መርሐቸዉም ይቃረናሉ። በስልጣን ግል እኩል ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/FnFK
ነገ-ይለያልምስል picture-alliance/dpa
ነሐሴ አራት 1961 (ዘመኑ በሙሉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ከኬንያዊዉ ተማሪ አይኑን ባይኑ በማየቱ ፌስታ ሲቦርቅ፣ ጄኔራል አባታቸዉን የተኩት ጄኔራል ያያት አባቱ «ምትክ» ያሉት ፓይለት የመጀመሪያዋን አዉሮፕላን በመከስከሱ ሐዘን ተክዘዉ ነበር።የሩቅ-ለሩቆቹ አባቶች ዉልዶች በርግጥ የአንድ ሐገር ዜጎች ናቸዉ።ግን የሁለት-ዘመን የሁለት አለም ሰዎች።እሳቸዉ ከብሪታንያ-አየርንድ የሚመዘዝ ባሪያ ፈንጋይ፣ ቅኝ ገዢ፣ አገር አቅኚ፣ ዘራቸዉን ይቆጥራሉ።እኚሕኛዉ የብሪታንያ ቅኝ ተገዢ፣ የቅኝ ገዢዎች አገልጋይ ዉላጅ እያሉ ከነጩ ይቀያጣሉ።እንደ ዘር፣ ትዉልዳቸዉ ሁሉ በአስተሳሰብ መርሐቸዉም ይቃረናሉ። በስልጣን ግል እኩል ናቸዉ። ሴናተሮች።ላንድ-ስልጣን ይሻኮታሉ።መኬይ እና ኦባማ ።ማን ያሸንፍ ይሆን? እስከ ነገ ዉድቅት እንጃ እያልን በማንነት፣ እንዴትነታቸዉ ጥቂት እንቆዝም አብራችሁኝ ቆዩ።