1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስ አስከፊ የአየር ሁኔታ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 19 2008

ደቡባዊውን፣ማዕከላዊውንና ምዕራባዊውን የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች እያጠቃ ያለው ኃይለኛ ወጀብና ንፋስ አዘል አስከፊ የአየር ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

https://p.dw.com/p/1HVlr
USA Unwetter Tornado Texas
ምስል picture-alliance/dpa/M. Stone

[No title]

ኤልኒኞ በተባለው የባህር ሙቀት መጨመር ምክንያት ሳይከሰት አልቀረም የተባለው ከፍተኛ ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ(ቶርኔዶ) እና በረዷማ ዝናብ በቴክሳስ፣ ሚዙሪ እና ምዕራባዊው የኢሊኖይስ ግዛት በአንድ ሳምንት ውስጥ የ43 ሰዎች ህይወት ቀጥፏል።በ ሺዎች የሚገመቱ ቤቶች ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን በመቶ ሺዎች የሚገመቱ አባወራዎች የመብራት አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል። ትናንት ሰኞ ደግሞ በመላው ዩናይትድስቴትስ 1165 የአውሮፕላን በረራዎች ተሰርዘዋል። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ

እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሰ