1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስ የአጋማሽ ጊዜ የምርጫ ፉክክር

ሰኞ፣ ጥቅምት 24 2007

በዩናይትድ ስቴትስ ነገ በሚካሄደዉ የአጋማሽ ምርጫ ከወዲሁ የትኛዉ ፓርቲ የት ድል ሊቀናዉ እንደሚችል ትንበያ እየተሰጠ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1DgIe
USA Wahlen Kongresswahlen Info-Blatt in Colorado Leitfaden
ምስል Reuters/R. Wilking

በዚሁ መሠረትም በሚካሄደዉ የተወካዮች ምክር ቤትና የሴኔት የማሟያ ምርጫ ሪፐብሊካኖች የላይኛን ምክር ቤት እንደሚረከቡ ይጠበቃል። በተለይም በርካታ ድምፅ ይገኝባቸዋል ከሚባሉ ግዛቶች የተሰበሰበዉ የሕዝብ አስተያየት መመዘኛ ቀመር ሚዛኑ ለሪፐብሊካን ያጋደለ መሆኑን አመላክቷል። ዴሞክራቶች በሴኔቱ ያላቸዉን የበላይነት ለማስጠበቅ ያደረጉት ጥረት በድል የመጠናቀቁ ነገር አጠራጣሪ እንደሆነ ነዉ የሚገመተዉ። ምርጫዉ ሪፐብሊካኖች አላላዉስ ባሏቸዉ የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ፖሊሲዎችና ቀጣይ አጀንዳዎች ላይ የሚኖረዉ አንድምታ ምን ይሆን? የዕለቱን የማኅደረ ዜና ጥንቅር ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ፤

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ