1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ መርሕ      

ሐሙስ፣ ኅዳር 16 2014

በሞርጋን ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ኘሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ እንዳሉት የፖሊሲው ዋነኛ ግብ የአሜሪካንን ጥቅም ማስከበር ነው።

https://p.dw.com/p/43UBl
Raychelle Omamo und Antony Blinken
ምስል Andrew Harnik/Pool/AP/picture alliance

የዩናይትድ ስቴትስ አዲስ መርሕ ስለአፍሪቃ

አሜሪካ በቅርቡ ይፋ ያደረገችው የአፍሪቃ መርሕ ወይም ፖሊሲ ለአህጉሪቱ ብዙ አዲስ ነገር  አለመምጣቱን አንድ የፖለቲካ ሳይንስ ምሑር አመለከቱ::በሞርጋን ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ኘሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ እንዳሉት የፖሊሲው ዋነኛ ግብ የአሜሪካንን ጥቅም ማስከበር ነው::ይሁንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በቅርቡ በሦስት የአፍሪካ ሃገሮች ጉብኝት ማድረጋቸው ዩናይትድ ስቴትስ ከአህጉሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል  ፍላጎት እንዳላት አመላካች መሆኑን ኘሮፌሰር ጌታቸው ተናግረዋል::

ታሪኩ ኃይሉ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ