1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የዩናይትድ ስቴትስ ፖለቲካዊ ቀዉስ

ዓርብ፣ ሰኔ 2 2009

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸዉ ወቅት ከሩሲያ ተደርጎላቸዋል ተብሎ የሚጠረጠረዉ ድጋፍ እንዳይጣራ ለማድበስበስ ብዙ መሞከራቸዉን የቀድሞዉ የሐገሪቱ ብሔራዊ የምርመራ ቢሮ (FBI) ኃላፊ አጋለጡ።

https://p.dw.com/p/2eQed
USA Comey Anhörung
ምስል picture-alliance/dpa/AP/J. S. Applewhite

 

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸዉ ወቅት ከሩሲያ ተደርጎላቸዋል ተብሎ የሚጠረጠረዉ ድጋፍ እንዳይጣራ ለማድበስበስ ብዙ መሞከራቸዉን የቀድሞዉ የሐገሪቱ ብሔራዊ የምርመራ ቢሮ (FBI) ኃላፊ አጋለጡ። ትራምፕ ከሥልጣን ያባረሯቸዉ ጄምስ ኮሜይ ለሐገሪቱ ሴኔት የስለላ ጉዳይ ኮሚቴ እንደነገሩት ምርመራዉ እንዲድበሰበስ ፕሬዝደንቱ በተደጋጋሚ አሳስበዋቸዉ ነበር። ከሥልጣን የተባረሩትም የፕሬዝደንት ትራምፕን ጥያቄና ማሳሰቢያ አልቀበልም በማለታቸዉ እንደሆነ የቀድሞዉ የFBI ኃላፊ አስታዉቀዋል። የዋሽግተን ዲሲዉ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሃመድ 

ሸዋዬ ለገሠ