1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኔስኮ የቻይና አደራ ፈንድ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 9 2006

ቻይና 8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ያደረገችበት የዚሁ የዩኔስኮ የቻይና አደራ ፈንድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ከሆኑት ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት ።

https://p.dw.com/p/1BkPQ
UNESCO United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization Logo

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት UNESCO ከህዝባዊት ቻይና ሪፐብሊክ መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በ 8 የአፍሪቃ ሃገራት የመምህራን ሥልጠና ፕሮጀክት እያካሄደ ነው ። ቻይና 8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ያደረገችበት የዚሁ የዩኔስኮ የቻይና አደራ ፈንድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ከሆኑት ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት ። ፕሮጀክቱ በዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች የመምህራን ማሰልጠኛዎችን ብቃት ከፍ የማድረግ እቅድ አለው ። ፕሮጀክቱ የሃገሪቱን የትምህርት ጥራትም በማሳደግም ረገድ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የፓሪስዋ ወኪላችን የሃይማኖት ጥሩነህ ዘገባ ያስረዳል ።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ