1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኤስ አሜሪካ ምርጫ አሸናፊ ባራክ ኦባማ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 27 2001

በጉጉት ሲጠበቅ የቆየው የዩኤስ አሜሪካ ምርጫ በባራክ ኦባማ አሸናፊነት መጠናቀቁን አሜሪካውያን በከፍተኛ ደስታ ተቀብለውታል።

https://p.dw.com/p/Fo41
ባራክ ኦባማ እና ቤተሰባቸው ከድል በኋላ
ባራክ ኦባማ እና ቤተሰባቸው ከድል በኋላምስል AP

ባራክ ኦባማ የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ፕሬዚደንት ሆነው መመረጣቸው ትልቅ ፋይዳ እንዳለው፡ በተለይ ኦባማ ለውጥ ብለው ይዘውት የተነሱት መፈክራቸው በፕሬዚደንት ጆርጅ ዳብልዩ ቡሽ ስምንት የስልጣን ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተበላሸውን የሀገሪቱን ገጽታ እንደሚያሻሽለው ብዙዎች ይገምታሉ።
የአፍሪቃ ሕብረትና ኢትዮጵያስ ስለኦባማ ድል ያላቸው አስተያየት ምን ይመስላል ?