1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኤስ አሜሪካ፡ የፓኪስታን እና የአፍጋኒስታን ፕሬዚደንቶች ምክክር

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 29 2001

ታሊባኖችና አል ቓይዳ በፓኪስታንን ከአፍጋኒስታን ጋር በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ተጽዕኖአቸውን እያጠናከሩ መምጣታቸው ያሳሰባቸው የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ትናንት በዋሽንግተን ከፓኪስታን እና ከአፍጋኒስታን ፕሬዚደንቶች አሲፍ አሊ ዛርዳሪና ሀሚድ ካርዛይ ጋር የሶስትዮሽ ምክክር አካሄዱ።

https://p.dw.com/p/HlGi
በጸረ ሽብርተኝነት ትግል ትብብራቸውን ያጠናከሩት ኦባማ፡ ካርዛይና ዛርዳሪ
በጸረ ሽብርተኝነት ትግል ትብብራቸውን ያጠናከሩት ኦባማ፡ ካርዛይና ዛርዳሪምስል AP

ሁለቱ ሀገሮች ታሊባንን እናና አል ቓይዳን ለመታገል ለጀመሩት ጥረታቸው ዩኤስ አሜሪካ የምታቀርብላቸው የገንዘብና የጦር ርዳታ ወደፊትም እንደሚቀጥል ፕሬዚደንት ኦባማ በዚሁ ወቅት ለፓኪስታንና ለአፍጋኒስታን አቻዎቻቸው አረጋግጠውላቸዋል። በዚሁ ውይይት ላይ የሶስቱ ሀገሮች የመከላከያ፡ የውጭ ጉዳይ፡ የደህንነት ሚንስትሮች እና ሌሎች ከፍተኛ ዲፕሎማቶችም ተካፋዮች ነበሩ።

አበበ ፈለቀ/አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሐመድ