1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት የመካከለኛ ምስራቅ ጉዞ

ረቡዕ፣ ግንቦት 26 2001

የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ዛሬ ሳውዲ ዐረቢያ ርዕሰ ከተማ ሪያድ ገቡ።

https://p.dw.com/p/I2lU
ምስል AP

ይኸው አሜሪካዊው ፕሬዚደንት ዛሬ በሳውዲ ነገ ደግሞ በግብጽ የሚያደርጉት ጉብኝታቸው ከሙስሊሙ ዓለም ጋር ስልጣን ሲይዙ እንደሚጀምሩት ያስታወቁትን ውይይት መቀጠላቸውን አሳይቶዋል። ኦባማ ነገ በግብጽ የሚያሰሙት በትልቅ ጉጉት የሚጠበቀው ዲስኩራቸው የምዕራቡንና የሙስሊሙን ዓለም ግንኙነት ለማቀራረብና በሁለቱ ወገኖች የሚታዩ አንዳንድ አለመግባባቶችን ለማስወገድ እንደሚረዳ ተገምቶዋል። ሆኖም፡ አበበ ፈለቀ ያነጋገራቸው አንድ ተንታኝ እንደሚሉት የፕሬዚደንት ኦባማ ዲስኩር ብቻውን ለሁሉም ችግሮች መፍትሄ ያስገኛል ተብሎ ሊታሰብ አይገባም።

የፕሬዚደንት ኦባማ ዲስኩር እክል በገጠመው የእስራኤላውያን የፍልስጤማውያን የሰላም ድርድር ላይ እንደሚያተኩር ይገመታሉ። ሆኖም፡ ዜናነህ መኮንን በላከው ዘገባ መሰረት፣ ኦባማ ትኩረታቸውን በዐረቡ ዓለም በሚታየው የሰብዓዊ መብት አያያዝ መሆን እንዳለበት ነው ከመግለጽ አልተቆጠቡም።

AF/ZM/AA