1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩክሬን ቀዉስ፤የኔቶ ዝግጅትና ዲፕሎማሲ

ዓርብ፣ ጥር 29 2007

የጀርመንና የፈረንሳይ መሪዎች በበኩላቸዉ አዲስ የነደፉትን የሠላም ዕቅድ ለዩክሬንና ለሩሲያ መሪዎች ለማስረዳት ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ላይ ናቸዉ።አንዳድ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ባንፃሩ በምሥራቃዊ ዩክሬኑ ጦርነት ሽንፈት የገጠመዉን የኪየቭን መንግሥት ከዉድቀት ለማዳን ማስታጠቅ አለብን ይላሉ

https://p.dw.com/p/1EXNx
ምስል AFP/Getty Images/J. Thys

የሰሜን አትላቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) ፈጥኖ የሚወረወር አዲስ ጦር እንዲመሠርትና እስካሁን «አፀፋ ሠጪ» ተብሎ የሚጠራዉ ግብረ-ሐይሉ ወታደሮች ቁጥር ከ13 ሺሕ ወደ 30 ሺሕ ከፍ እንዲል ወስኗል።ትናንት ብራስል ተሰብሰበዉ የነበሩት የጦር ተሻራኪዉ ድርጅት አባል ሐገራት መከላከያ ሚንስትሮች አዲሱን ዉሳኔ ያሳለፉት እየከፋ የመጣዉ የዩክሬን ጦርነት ሥላሳሰባቸዉ እንደሆነ አልሸሸጉም።የጀርመንና የፈረንሳይ መሪዎች በበኩላቸዉ አዲስ የነደፉትን የሠላም ዕቅድ ለዩክሬንና ለሩሲያ መሪዎች ለማስረዳት ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ላይ ናቸዉ።አንዳድ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ባንፃሩ በምሥራቃዊ ዩክሬኑ ጦርነት ሽንፈት የገጠመዉን የኪየቭን መንግሥት ከዉድቀት ለማዳን ማስታጠቅ አለብን ይላሉ።የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ