1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የያራ ሽልማት ያገኙት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ፤

ዓርብ፣ ነሐሴ 30 2006

ኢትዮጵያዊዉ የአፈር ሳይንስ ባለሙያና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ የኖርዌይን ዓለም ዓቀፍ ሽልማት ተቀበሉ። ሽልማት ሰጪዉ ተቋም በድረገፁ ላይ ባሰፈረዉ መረጃ መሠረት ተሸላሚዉ ፕሮፌሰር ተካልኝ የተማሩትን ትምህርት ከአካዳሚ ሚናዉ ባለፈ ለኅብረተሰብ ትልቅ ጥቅም ለሚያስገኝ ዉጤት ማዋሉ ተሳክቶላቸዋል።

https://p.dw.com/p/1D7pE
Preisverleihung Yara Prize Award 2014
ምስል DW/G. Tedla

በአሁኑ ጊዜ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ እና የሚኒስትሩ አማካሪ የሆኑት የአፈር ሳይንስ ተመራማሪ ባካሄዱት የምርምር ተግባርም ለምነቱን ያጣ 13 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግም ማድረጋቸዉና ሌሎችም ስኬቶቻቸዉ ተዘርዝረዋል። ተመራማሪዉ በበኩላቸዉ ላለፉት ለሶስት አስርት ዓመታት በዘርፉ የሠሩ ሲሆን ከግብርና ጋ በተገናኘ የኢትዮጵያ ቁልፍ የሚባሉ ችግሮች እንዲታወቁና መፍትሄም እንዲያገኙ ጥረት ማድረጋቸዉን የያራን ሽልማት በተቀበሉት ወቅት ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ