1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደሞዝ ጭማሪውና የሠራተኛው አስተያየት

ሐሙስ፣ ጥር 19 2003

የኢትዮጵያ መንግስት ከያዝነው ጥር ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ከ 35 እስከ 39 በመቶ የሚደርስ የደሞዝ ጭማሪ ማድረጉን ትናንት አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/Qw2r
ምስል Fotolia/Joachim Wendler

የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ጁነዲን ሳዶ ትናንት በሰጡት መግለጫ ጭማሪው የፌደራልና የክል መንግስት መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች የፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የመንግስት ተሿሚዎችንና የህዝብ እንደራሴዎችን እንዲሁም የዳኝነት አካላትን እንዲሚያካትት አስታውቀዋል ። ዶቼቬለ ካነጋገራቸው ሰራተኞች አንዳንዶቹ መንግስት የኑሮ ውድነት ማካካሻ ያለው የደሞዝ ጭማሪ የሚያመጣው ለውጥ የለም ብለዋል ። አንዳንዶች ደግሞ ከደሞዝ ጭማሪው ጋር ተያይዞ የፍጆታ ዕቃዎች ዋጋ ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል ።

ታደሰ እንግዳው

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ