1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደራሲዉ ስንብት-ስብሃት

ሐሙስ፣ የካቲት 15 2004

በጾም መባቻ ዘወረደን አልፈን፣ ስብሃት ለእግዚአብሄር ብለን ተደስተን፣ ምድራዊ ጥበብንም ጨምረን እንጾማለን፣ ስብሃት አርፎአልና እርስዋን ያስተማረን። « እንግዲህ ጥበብን እንጹም» ይላል የአብይ ጾም መያዣ እና የስብሃት ከዚህ አለም በምት መለየት ስለገጠመብኝ የጻፍኩት ነዉ ያለዉ ግጣሚ እና የአስብሃት አድናቂ ደስታ ወገኛዉ።

https://p.dw.com/p/1498g
ምስል AP

በጾም መባቻ ዘወረደን አልፈን፣ ስብሃት ለእግዚአብሄር ብለን ተደስተን፣ ምድራዊ ጥበብንም ጨምረን እንጾማለን፣ ስብሃት አርፎአልና እርስዋን ያስተማረን።

« እንግዲህ ጥበብን እንጹም» ይላል የአብይ ጾም መያዣ እና የስብሃት ከዚህ አለም በምት መለየት ስለገጠመብኝ የጻፍኩት ነዉ ያለዉ ግጣሚ እና የአስብሃት አድናቂ ደስታ ወገኛዉ።

በሰነ-ፅሁፍ ባለሞያዎች የአጭር ልብ ወለድ አባት በመባል የሚደነቀው አንጋፋዉ ደራሲና ጋዜጠኛ ስብሃት ለአብ ገብረእግዚሃብሄር ብዙዎች እንደምንጠራዉ ጋሼ ስብሃት በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት በዋና አዘጋጅነት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ጋዜጦችና መፅሄቶች በአማርኛና በእንግሊዘኛ በየጊዜው የፃፈ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሃያሲ ነበር። በፈረንሳይና በዩናይትድ ሰስቴትስ ዩኒቨርስቲዎች እንደተማረም ይነገረለታል። ስብሃት ለየት ባለዉ አፈንጋጭ ጽሁፎቹ በቀደምቶቹ ዘመናት የህትመት ፈቃድ ተነፍጎአቸዉ ከሁለት እስርተ እመታት በላይ ቆይተዉ ለአንባቢ ባየደረሱም፣ ጽሁፎቹ ግዜን ጠብቀዉ በወጣት ባዛዉንቱ መወደሳቸዉ መወደዳቸዉ ገሃደ ነዉ። የኢትዮጽያ የስነ-ጽሁፍ ታሪክ ሲንሳ የስብሃት ብዕር በመጀመርያ ደረጃ ሊጠቀስ ይግባዋል ይላሉ አደናቂዎቹ። ትግራይ አድዋ አዉራጃ የተወለደዉ አንጋፋዉ ደራሲና ጋዜጠኛ ስብሃት ከሃምሳ አመት በላይ የቆየባቸዉ በጥበብ የተዋቡት የድርሰት እና የጋዜጠኝነት በረከቶች በአዲስ የአፃፃፍ ፈለግ እንድንማርበት ትቶትልን ስሙን በኢትዮጵያ ስን-ጽሁፍ የታሪክ ማህድር ተክሎ በህጻን በአዋቂዉ ጋሼ ተብሎ በስባ ስድስት አመቱ የካቲት አስራአንድቀን 2004 ዓ,ም ለሊቱን ላይመለስ አሸለበ። ነፍስ ይማር ፥ ለወዳጅ ዘመደ መጽናናትን ይስጥ እንላለን። ደራሲ ስብሃት ግብረ እግዚአብሄር፣ ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ በቆየባቸዉ በድርሰት እና በጋዜጠኝነት በረከቶች ዙርያ ባልንጀሮቹን እና የሞያ አጋሮቹን አነጋግረን በለቱ የባህል መድረክ ዝግጅት አቀናብረን ይዘናል! ሙሉዉን መሰናዶ ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ