1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ዓቀፍ የኤድስ ጉባኤ ፍጻሜ

ዓርብ፣ ሐምሌ 15 2008

ይኽው ጉባኤ ከፀረ ኤች አይቪ ኤድስ ዘመቻ መዳከም አንስቶ ፣ እስከ የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ መድሐኖቶች ዋጋ መናር ድረስ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ መክሯል ።

https://p.dw.com/p/1JUHx
Ban Ki-moon und Charlize Theron auf der Pressekonferenz der International AIDS Conference 2016
ምስል picture-alliance/dpa

[No title]


ከዚህ ሳምንት ሰኞ አንስቶ ደርባን ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ሲካሄድ የቆየው 21 ኛ ዓለም ዓቀፍ የኤድስ ጉባኤ ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ። ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ ሳይንቲስቶች ፣ ፖሊሲ አውጭዎች ፣ የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት የሚጥሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተወካዮች የተካፈሉበት ይኽው ጉባኤ ከፀረ ኤች አይቪ ኤድስ ዘመቻ መዳከም አንስቶ ፣ እስከ የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ መድሐኖቶች ዋጋ መናር ድረስ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ መክሯል ። ጉባኤው በተካሄደባት በደቡብ አፍሪቃ በየሳምንቱ እድሚያቸው ከ15 እስከ 24 የሚሆን ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ወጣት ሴቶች በኤች አይ ቪ ኤድስ ይያዛሉ ። ከ18 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ስለተገኙበት ስለዚህ ጉባኤ ጉባኤው ሂደት እና ከጉባኤው ፍፃሜ ምን እንደሚጠበቅ የጆሃንስበርጉን ተባባሪ ዘጋቢያችንን መላኩ አየለን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ። በቅድሚያ ጉባኤው ትኩረት ሰጥቶ የተነጋገረባቸውን ዐበይት ጉዳዮች ይነግረናል ።

መላኩ አየለ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ