1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ህዝበ ውሳኔ እና እንዳያስከትል ያሰጋው ስደት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 13 2003

የደቡብ ሱዳን ህዝብ እአአ የፊታችን ጥር ዘጠኝ ቀን የግዛቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ህዝበ ዉሳኔ/ሬፈረንደም/ ያካሂዳል።

https://p.dw.com/p/QipA
ምስል picture alliance/dpa

የተፈናቀሉ እና በጎረቤት ሀገሮች በስደት የነበሩ ደቡብ ሱዳናውያን በወቅቱ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው በመመለስ በህዝበ ውሳኔው ለመሳተፍ ተመዝግበዋል። በዚህም ደቡብ ሱዳናውያኑ ከሱዳን ተገንጥለዉ ነጻ መንግስት እንደሚመሠርቱ ብዙ የፖለቲካ ታዛቢዎች ግምታቸውን ገልጸዋል። ይህም፡ በሰሜንና በደቡብ ሱዳን መካከል አዲስ ውዝግብ ሊያስነሳ፤ ብዙ የደቡብ ሱዳን ተወላጆች ወደ ጎረቤት ሀገሮች እንዲሸሹ ሊያስገድድ እንደሚችል አንዳንድ ተንታኞች ይናገራሉ። ይህ ዓይነት ሁኔታ ቢፈጠር የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መስሪያ ቤት አስፈላጊውን ርዳታ ለማቅረብ ዝግጁ መሆኑን አርያም ተክሌ ያነጋገረቻቸው የድርጅቱ ቃል አቀባይ ፋቱማታ ንዣንካምቦ አመልክተዋል።

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ