1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ስደተኞችና ኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ሰኔ 26 2006

በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ዜጎች አሁንም ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸዉን መቀጠላቸዉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ «ዩ ኤን ኤች ሲአር»

https://p.dw.com/p/1CVQq
ምስል DW/Coletta Wanjoyi

እና የዓለም ምግብ ድርጅት፣ « ዳብል ዩ ኤፍ ፒ » በየፊናቸዉ እንዳሉት የደቡብ ሱዳን ሁኔታ ብዙም ባለመለወጡ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ተጨማሪ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸዉ አይቀርም።የሁለቱ ድርጅቶች ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ተጨማሪ ርዳታ ካለገኙ እስካሁን ኢትዮጵያ ለገቡትም ሆነ ወደፊት ለሚገቡት ስደተኞች የሚያበሉት አይኖራቸዉም።

Südsudan Zivilisten auf der Flucht in Bentiu
ምስል Reuters

ኢትዮጵያ-የዓለም ምግብ ድርጅት « ዳብልዩ ኤፍ ፒ » ሐላፊ አብዱ ዲንግ እንደሚሉት ለሥደተኞች «የክፍት በር መርሕ» በመከተሏ-የአካባቢዉ ሐገራት ዜጎች በገፍ-እየተሰደዱባት ነዉ። በኢትዮጵያ የሌላዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅ-የስደተኞ ከፍተኛ ኮሚሽነር «ዩ ኤን ኤች ሲአር » ሐላፊ ቦርንዌል ካንታንዴ---ከስድስት ዓመት በፊት-ኢትዮጵያ ዉስጥ የበሩት ስደተኞች በአስር ሺሕ የሚቆጠሩ ነበሩ።አሁን ካንታንዴ-ይቀጥላሉ።

«6 ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ዉስጥ የነበሩት ስደተኞች ዘጠና ሺሕ አይሞሉም ነበር።አሁን ከግማሽ ሚሊዮን ይበልጣሉ።ከተወሰኑ አመታት በፊት ስምንት መጠለያ ጣቢዎች ነበሩ።አሁን በምንናገርበት ወቅት ግን ከ22 በላይ ጣቢያዎች አሉ።ስደተኛዉ እየጨመረ በመሆኑ ተጨማሪ ጣቢያ ያስፈልገናል።»

ሥደተኞቹ-የሶማሊያ፤ የኤርትራ፤ የሰሜንና ደብቡ ሱዳን፤ የታላላቆቹ ሐይቆች አካባቢ ዜጎች ናቸዉ።ካለፈዉ ታሕሳስ ወዲሕ ግን-ካንታንዴ እንደሚሉት ደቡብ ሱዳኖችን የሚያሕል የለም።

Sudanesische Flüchtlinge in Äthopien Flüchtlingslager
ምስል DW/Coletta Wanjoyi

«ካለፈዉ ታሕሳስ ጀምሮ ከ158 ሺሕ በላይ ስደተኞች ተቀብለናል።አሁንም ወደ ጋምቤላ አዳዲስ የሚመጡ እየተቀበልን ነዉ።በምንነጋገርበት ወቅት አሁን እንኳን 4 ሺሕ ሰደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ለመግባት አየጠበቁ ነዉ።ጋምቤላ ዉስጥ 3 ጣቢያዎች ከፍተናል።ሌሎች ተጨማሪ ስደተኞችን ለማስተናገድ ተጨማሪ ጣቢዎችን ለመክፈት ከመንግሥት ጋር እየጣርን ነዉ።»

ሶማሊያ በድርቅ በተመታችበት ወቅት-እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ2011 ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ የበነረዉ ስደተኛ ቁጥር-መቶ ሐምሳ ሺሕ የደረሰዉ ከሁለት ዓመት በኋላ ነበር።

የደቡብ ሱዳኑ ግን በስድስት ወር ከመቶ-ሐምሳ ስምት ሺሕ በልጧል።በዚሕ አልቆመም።ሕዝቡ አሁንም ይሰደዳል።በኢትዮጵ የዓለም ምግብ ድርጅት ሐላፊ አብዱ ዲየንግ እንደሚሉትማ ምዕራብ ኢትዮጵያ በስደተኞች ጎርፍ መጥለቅለቋ አይቀርም።«የደቡብ ሱዳን ሁኔታ አልተለወጠም።» ይላሉ ዲየንግከተለወጠም ረሐብ ይከሰታል የሚለዉ የብዙዎች ሥጋት ለዕዉነት መቃረቡ ነዉ።» ቀጠሉ ሐላፊዉ።እና ወደ ኢትዮጵያ የሚገባዉ ደቡብ ሱዳናዊ እስከ ጥር ድረስ ከ300 ሺሕ ይበልጣል።ዓለም አቀፉ ድርጅት ግን ለተጨማሪ ስደተኞች ቀርቶ አሁን ላሉት እንኳን ያለዉ ቀለብ-እስከ ጥቅምት ድረስ ቢያግደረድረዉ ነዉ።

«ለስደተኛዉ ያስቀመጥነዉ ሐብት ምንም ሆነ ምን አዳዲስ የሚመጡት ከዚያችዉ መካፈል አለባቸዉ።ሥለዚሕ አንተ እንደጠቀስከዉ የዓለም ምግብ ድርጅት ከጥቅምት በኋላ ምንም ምግብ አይኖረዉም።»

ስደተኛዉን ለመመገብ-የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተጨማሪ ርዳታ እየጠየቀ ነዉ።ኢትዮጵያ የሠፈሩ ደቡብ ሱዳኖችን ለመመገብ ዓለም አቀፉ ድርጅት በወር ሐያ ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገዋል።

ነጋሽ መሀመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ