1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በዩጋንዳ

ረቡዕ፣ መጋቢት 27 2009

ዩጋንዳ ወደ 3,000 የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን ዜጎች የሀገራቸው የመንግሥት ጦር አባላት በአንድ የድንበር ከተማ ላይ የሰነዘሩትን ጥቃት ሸሽተው ትናንት ወደ ሀገሯ መግባታቸውን ገለጸች። በሀገሩ ብዙ ስደተኞችን በማስተናገዱ ለሚታወቀው የዩጋንዳ መንግሥት ይህ ሁኔታ ትልቅ ተግዳሮት ሆኖበታል።

https://p.dw.com/p/2ajPg
Uganda Bürgerkrieg und Hunger im Südsudan treiben Menschen zur Flucht
ምስል Getty Images/D. Kitwood

Uganda refugees - MP3-Stereo

ምክንያቱም ስደተኞች አሁን በብዛት ሀገሩ በገቡበት ሁኔታ የተነሳ ለሁሉም ስደተኞች እንደሚፈለገው ርዳታ ለማቅረብ አቅሙ እና ገንዘብ እንደጎደለው አስታውቋል። 

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ወታደሮች ከዩጋንዳ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ በሚገኘው የፓጆክ ከተማ ላይ ጥቃት በመሰንዘር ብዙዎችን መግደላቸው ተሰምቷል። ወደ 3,000 የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን  ዜጎች የሱዳን ህዝብ አፃ አውጪ ጦር 50,000 ሰው በሚኖርባት ከተማ ባለፈው ሰኞ በየጣለውን ጥቃት ሸሽተው ትናንት ወደ ጎረቤት ዩጋንዳ ተሰደዋል። 
ዩጋንዳ በተመድ ዘገባ መሰረት፣ በዓለም ብዙ ስደተኞችን የምታስተናግድ ሀገር ናት፣ በቢዲ ቢዲ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ብቻ 274,000 ስደተኞች ይገናሉ። በዚህ ወር ብቻ 800,000 የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ዩጋንዳ የገቡ ሲሆን፣ ይህ በሀገሪቱ ስደተኞችን የማስተናገድ አቅም ላይ ትልቅ ተግዳሮት ደቅኗል። ይኸው አዲሱ የስደተኞች እንቅስቃሴ ሰሞኑን በፈነዳው ውጊያ ሰበብ ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ በተከሰተውም ረሀብ እና እየወደቀ ባለው የኤኮኖሚ ሁኔታም ምክንያት ነው።
ይኸው ሁኔታ የዩጋንዳን መንግሥት እና የርዳታ ድርጅቶችን አሳስቧል። «ዩኤንኤችሲአር» በዩጋንዳ መጠለያ ጣቢያዎች ያሉትን ስደተኞች በጠቅላላ ለመርዳት ቢያንስ 782 ሚልዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የግብረ ሰናዩ ድርጅት «ዎርልድ ቢዥን» የዩጋንዳ ቅርንጫፍ ኃላፊ ጂልበርት ካማንጋ ከሰሜን ዩጋንዳ ለዶይቸ ቬለ በስልክ እንዳሉት፣ ብዙዎቹ የርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማከናወን አልቻሉም።
« ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዩጋንዳ ያሉትን ስደተኞች ለመርጃ እንደሚፈለገው ርዳታ እየሰጡ አይደለም።  የዩጋንዳ መንግሥት ድጋፍ የሚሞገስ ቢሆንም፣ ስደተኞቹን ያስተናግድ ዘንድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግለት ጥሪ እናቀርባለን። ምክንያቱም፣ በዩጋንዳ ያሉት የርዳታ ድርጅቶች በጠቅላላ የበጀት እጥረት አጋጥሟቸዋል። »
በዚሁ ሰበብም ስደተኞች በቂ ርዳታ አልቀረበም በሚል ቅሬታ እያሰሙ መሆኑን አንዱ ገልጿል።
« የሚሰጡን ምግብ በቂ አይደለም። ለአንድ ለራስህ ከሆንክ 12 ኪሎ እህል ይሰጡሀል፣ ይህ ለአንድ ወር ነው። »
የአንዱ መጠለያ ጣቢያው ኃላፊ ባርያምዌሲጋ ሮበርት እንዳሉት፣ ድርጅቶቹ በቂ  ምግብ ስለሌላቸው ለስደተኞቹ የተወሰነ ምግብ ብቻ ነው የሚሰጡት። የ«ዩኤንኤችሲአር» ኃላፊ ፊሊፖ ግራንዴ ባለፈው ዓመት ዩጋንዳን በጎበኙበት ጊዜ ፣ ሀገሪቱ በየጊዜው ቁጥራቸው እየጨመረ የሄዱትን ስደተኞች ለማስተናገድ ችግር እንደገጠማት በመናገር ድጋፍ እንዲደረግላት ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
« መንግሥት እያቀረበ ያለውን ርዳታ እና ቨስደተኞች ቁጥር መጨመር በሄደበት ሰበብ  የገጠመውን ተግዳሮት ራሴ ለመመልከት ችያለሁ። ከዚህም በመነሳት ለጋሽ ሀገራት ተጨማሪ ርዳታ እንዲያቀርቡ እማፀናለሁ። »
ዩጋንዳ ስደተኞችን ማስተናገዷን እንደምትቀጥል ሮበርት ቢገልጹም፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የደቡብ ሱዳን ውጊያ የሚያበቃበትን እና ስደተኞች ወደ ትውልድ ሀገራቸው የሚመለሱበትን መንገድ መንገድ ቢያፈላልግ መልካም እንደሚሆን አስታውቀዋል።ከደቡብ ሱዳን ስደተኞች መካከል 86% ሴቶች እና ህፃናት ናቸው። 

Deutschland Treffen Steinmeier mit Filippo Grandi in Berlin
ምስል picture-alliance/dpa/R. Jensen
Südsudan Kämpfer
ምስል picture alliance/AP Photo/J. Lynch

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ