1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተንታኞች ስምምነቱ ለቀጠናው ላቅ ያለ አንደምታ አለው ይላሉ

ሰኞ፣ ሐምሌ 24 2009

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ባለፈው ጥቅምት ወር በጁባ በተለያዩ ዘርፎች የትብብር ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡ ከስምምነቶቹ መካከል በወታደራዊ እና ጸጥታ መስኮች የሚያደርጓቸው ትብብሮች ይጠቀሳሉ፡፡ የደቡብ ሱዳን ካቢኔ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባካሄደው ስብሰባ ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያደረገችውን ወታደራዊ ስምምነት ማጽደቁ ተዘግቧል፡፡

https://p.dw.com/p/2hT4v
Afrika Juba - Äthiopischer Premierminister Hailemariam Desalegn und südsudanischer Präsident Salva Kiir
ምስል Reuters/J. Solomon

ተንታኞች ስምምነቱ ለቀጠናው ላቅ ያለ አንደምታ አለው ይላሉ

ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ወታደራዊ ስምምነት የተፈራረሙት ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት ስነ ስርዓት ነበር፡፡ በወቅቱ ሁለቱም ሀገራት ነፍጥ ያነሱ ተቃዋሚ ቡድኖችን በየፊናቸው ላለመስጠለል ተሰማምተዋል፡፡ ወታደራዊ ስምምነቱ መጽደቁ ለሁለቱ ሀገራት እና ለቀጠናው ያለው አንደምታ እያጠያያቀ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ተቃናቃኝ ቡድኖችን የማደራደር እና የማስማማት ሚና ስታጫወት ቆይታለች፡፡ ከመንግስትም ሆነ በአማጽያን በኩል ገለልተኛ እንደሆነች ይታመን ነበር፡፡ በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ቀረቡ ከተባሉ ቅሬታዎች በኋላ ግን ኢትዮጵያ ወደ መንግስት ወገን የማዘንበል አዝማሚያ ይታያል የሚሉ ታዛቢዎች አሉ፡፡ በጥቅምት ወር የተፈረመው ወታደራዊ እና የጸጥታ ጉዳዮች ስምምነትንም ለዚህ በማሳያነት ያነሳሉ፡፡

እነዚህን ጉዳዮች በማንሳት ዶይቸ ቬለ በምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ጥናት የሚካሄዱትን አቶ አበበ አይነቴን አነጋግሯል፡፡ አቶ አበበ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ኢንስቲትዮት ውስጥ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለጥያቄዎቻችን የሰጡትን ምላሽ ለማዳመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፡፡       

 

ተስፋለም ወልደየስ

አርያም ተክሌ