1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ዉጊያና ኢጋድ

ሐሙስ፣ መጋቢት 4 2006

ኢትዮጵያ፤ኬንያ ብሩንዲና ሩዋንዳ ጦር ለማዝመት ወስነዋል።ጁቡቲም ጦር የማዝመቱን ጉዳይ እንደምታስብበት አስታዉቃለች።ዘመቻዉን ግን የአፍሪቃ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማፅደቅና የዘማቹን ጦር ወጪ መሸፈን አለባቸዉ

https://p.dw.com/p/1BPSs
ምስል picture-alliance/dpa

የምስራቅ አፍሪቃ በይነ መንግሥታት የልማት ባለሥልጣን አባል ሐገራት መሪዎች የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃላት ከዚሕ ቀደም የተፈራረሙትን የተኩስ አቁም ሥምምነት ገቢራዊነት የሚቆጣጠር ጦር ለማዝመት ተስማሙ።አዲስ አበባ ዉስጥ ዛሬ ዉሏቸዉን የመከሩት የሰባቱ አባል ሐገራት መሪዎች ባሳለፉት ዉሳኔ መሠረት እስከ ሚያዚያ አጋማሽ ድረስ ጦሩ ደቡብ ሱዳን ዉስጥ ይሰፍራል።ኢትዮጵያ፤ኬንያ ብሩንዲና ሩዋንዳ ጦር ለማዝመት ወስነዋል።ጁቡቲም ጦር የማዝመቱን ጉዳይ እንደምታስብበት አስታዉቃለች።ዘመቻዉን ግን የአፍሪቃ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማፅደቅና የዘማቹን ጦር ወጪ መሸፈን አለባቸዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ