1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ዉጥረትና የመብት ተሟጋች ተቋማት ጥሪ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 27 2007

ከ 50 የሚበልጡ የደቡብ ሱዳን ዜጎች፤ የሰብዓዊ ተቋማትና ፤ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት እንዲሁም የደቡብ ሱዳን ጎረቤት ሃገራት የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ላይ አስቸኳይ የጦር መሳርያ ማዕቀብ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ።

https://p.dw.com/p/1DiZx
Human Rights Watch Logo

ተቋማቱ ይህን ጥሪ ያቀረቡት ጎረቤት ሃገራቱ በደቡብ ሱዳን አንድ ዓመት በዘለቀዉ በየርስ በርስ ጦርጦርነት በሀገሪቱ የሚታየዉን አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቆም የተመድ የጸጥታ ምክርቤት በደቡብ ሱዳን የጦር መሳርያ ንግድ ማዕቀብ እንዲያደርግ ግፊት እንዲያደርጉ ነዉ። የጦር መሳርያ ማዕቀብ እንዲያደርግ ጥሪ መቅረቡን በተመለከተ የዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮዉን አነጋግረናል።

አንድ ዓመት በሆነዉ የደቡብ ሱዳኑ የርስበርስ ጦርነት እስካሁን አስር ሺ ሰዎች ሞተዋል፤ ከነዚህ መካከል ደግሞ አብዛኛዉ ሲቪል ነዉ። በጦርነቱ 1, 8 ሚሊዮን ህዝብ ከቤት ንብረቱ እንዲፈናቀል ተገድዋል። ጦርነቱን የሚያካሂዱት ሁለቱ ቡድኖች በጦርነቱ ቀላልና አነስተኛ የጦር መሳርያዎችንና የተለመዱ ወታደራዊ መሳርያዎችን እንደሚጠቀሙ ተመልክቶአል። በደቡብ ሱዳን በሲቢሉ ላይ የቀጠለዉ ጥቃት የሰብዓዊ ቀዌስ ማስከተሉንም ለጸጥታ ምክር ቤቱ ጥሪ ያቀረቡት ተቋማት ገልፀዋል። የሰብዓዊ ተቋማቱ ፤ የደቡብ ሱዳን ጎረቤት ሃገራት የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ላይ አስቸኳይ የጦር መሳርያ ማዕቀብ እንዲያደርግ ጥሪ ማድረጋቸዉ ፋይዳዉ ምን ይሆን? በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮ ጉዳዩ ይላሉ፤
«ጉዳዬ ተቀናቃኝ ኃይላቱ በሲቪል ነዋሪዎች ላይ ከባድ ጥቃት እያደረሱ ነዉ። እነዚህ ኃይላት የጦር ወንጀል ፈፅመዋል፤ በሰብዓዊነት ላይም የጦር ወንጀል እያደረሱም ይሆናል። ስለዚህ ፊርማ በማሰባሰብ የተመድ ጸጥታዉ ምክር ቤት የጦር መሳርያ ማዕቀብ እንዲያደርግ ዋና ለዚህ ወንጀል ኃላፊነት ያለበት እያንዳንዱ አመራር ላይ የተለያየ ማዕቀቦችን እንዲጥል ነዉ»
ለአንድ ዓመት የዘለቀዉ የደቡብ ሱዳን የርስ በርስ ጦርነትነትን ለመግታት የተለዩ የሰላም ድርድሮች ተካሂደዋል፤ ጦርነቱንም ለማቆም ዉሎች ተፈርመዋል እንዲያም ሆኖ ጦርነቱ መቋጫ ያጣ ይመስላል። እንደ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮ ተቀናቃኝ ኃይላቱ ሰላም ለማምጣት እጅግ ፋላጎት የላቸዉም፤
« እንደሚታየዉ ከሆነ የደቡብ ሱዳኖቹ ተቀናቃኝ ኃይላት ሰላም ለማምጣት እጅግም ፍላጎት ያላቸዉ አይመስልም፤ በአንፃሩ ከባድ ጦርነቱን ቀጥለዋል። በዚህ ጦርነት ስር የጥቃት ዋንኛ ተጎጅዎች በሁለቱም ወገን የሚገኙት የሲቪሉ ማኅበረሰብ ወገኖች ሆነዋል። የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዉ ድርጅት ሂዉማን ራይትስ ዎች እና ሌሎች ተቋማት ይህን ችግር ለመቀነስ እና የጦርነቱ ተፅእኖ በሲቪል ማኅበረሰቡ ላይ እንዳያይል የጦር መሳርያ ማዕቀብ ማድረግ ሳረፍ እጅግ ትክክለኛ መንገድ መሆኑን ያምናል። »
የደቡብ ሱዳኑን የርስ በርስ ጦርነት በተመለከተ የኬንያ የዩጋንዳና የኢትዮጵያ ፕሪዚዳንትና የአካባቢዉ ሃገራት መሪዎች ዛሬ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በየነ መንግሥታት ሃገራት ኢጋድ አዲስ አበባ ላይ ባዘጋጃዉ ስብሰባ ላይ ተካፍለዋል። ፊርማ በማሰባሰብ ጥሪ ያቀረቡት ሰብዓዊ ተቋሞች የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይላት መካከል በተደረገዉና የተኩስ አቁም ሥምምነትን በተመለከተ እና በተቀናቃኝ ወገኖች መካከል በሚደረገዉ ጦርነት የተፈፀሙትን የጦር ወንጀሎች ኢጋድ በይፋ ዘገባ እንዲያቀርብ ጠይቀዋ። ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ከተደረገዉ ስብሰባ ምን ፍሪ ነገር ይገኛ ተብሎ ይጠበቅ ይሆን? እንደ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር እንደ ሌስሊ ሌፍኮ
« በደቡብ ሱዳን የርስ በርስ ጦርነት የሚያካሂዱት ሁለቱ ቡድኖች ማለት የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና እና የተቃዋሚዉ የሪክ ማቻር ወገኖች በሲቪሉ ላይ እያደረሱ የለዉን ጥቃት እንዲያቆሙና ግፊት ለማድረግ በሀገሪቱ ያለዉን ዉጥረት ለመቅረፍ ትርጉም ያለዉ ርምጃ በማድረጉ ረገድ የአካባቢዉ ሃገራት ማለትም ኢትዮጵያ ኬንያ እና ዩጋንዳ ወሳኝ ሚና አላቸዉ። ስለዚህም የአካባቢዉ ሃገራት እና ኢጋድ በደቡብ ሱዳን የሚታየዉን ጭፍጨፋ ለመግታት ያላቸዉን ሚና ተጠቅመዉ መስራት ይኖርባቸዋል። ይህን ማድረግ ደግሞ የሚችሉት በተመድ የፀጥታዉ ምክርቤት ሊደረግ የሚችለዉን ማዕቀብ በመደገፍ ነዉ። በርካታ የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች የባንክ ሂሳብ፤ ሃብትና ንብረት በኬንያና በዩጋንዳ በመሳሰሉት ሃገራት አልዋቸዉ። ስለዚህም ይህን የጦር መሳርያ ማዕቀብ እንደረግ ጥረትና ድጋፋቸዉን ቢያሳዩ ይህን ከባድ ጦርነት በሚያደርጉት ወገኖች ላይ ትክክለኛ ተፅኖ ሊያመጣ ይችላል»
መቀመጫቸዉን በአፍሪቃና አዉሮጳ ያደረጉ 50 የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፊርማ በማሰባሰብ የደቡብ ሱዳን ጎረቤት ሃገራት የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ላይ አስቸኳይ የጦር መሳርያ ማዕቀብ እንዲያደርግ ጥሪ አቀርብዋል። ዩኤስ አሜሪካም በሁለቱም የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ወገኖች በኩል በሚገኙ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀም ማሳረፍ መጀመርዋ ይታወቃል።
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ

Äthiopien Friedensverhandlungen über Südsudan in Addis Ababa
ምስል ZACHARIAS ABUBEKER/AFP/Getty Images
Südsudan UN Treffen 12. August
ምስል Reuters
Äthiopien Friedensverhandlungen über Südsudan in Addis Ababa
ምስል ZACHARIAS ABUBEKER/AFP/Getty Images