1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ አፍሪቃ ገዢ ፓርቲ ምርጫ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 10 2005

ዙማ ጉባኤዉን ሲከፍቱ ሕዝባቸዉንና ባለሐብቶችን ለማረጋጋት ሞክረዋል።ሐገራቸዉ አደጋ እንደማይገጥማት፥ ፓርቲያቸዉም የአፍሪቃን ምጣኔ ሐብት የምትመራዉን ሐገር መምራቱ እንደማይገደዉ አስታዉቀዉ ነበር።ተንታኞች ግን በዚሕ አይስማሙም።

https://p.dw.com/p/175l2
Supporters of President Jacob Zuma celebrate as delegates to the National Conference of the ruling African National Congress (ANC) begin voting for their leadership in Bloemfontein, December 17, 2012. Zuma is being challenged by his deputy Kgalema Motlanthe for the position of President of the party which has ruled South Africa since the country's first democratic elections in 1994. REUTERS/Mike Hutchings (SOUTH AFRICA - Tags: POLITICS ELECTIONS)
ቅስቀሳዉምስል Reuters

19 12 12


የደቡብ አፍሪቃዉ ገዢ ፓርቲ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት (ANC) ጠቅላላ ጉባኤ በሥልጣን ላይ ያሉትን ጄኮብ ዙማን ለተጨማሪ ዘመን የፓርቲዉ ፕሬዝዳት አድርጎ መርጧቸዋል።ዙማ በድጋሚ የተመረጡት በፓርቲዉ አመራር መካካል ያለዉን ሽኩቻ፥በአመራር ድክመትና በሙስና የሚሠነዘርባቸዉን ወቀሳና ትችት አልፈዉ ነዉ።በፓርቲዉ ደንብ መሠረት የፓርቲዉን የፕሬዝዳትነት ሥልጣን የሚይዝ ለሐገሪቱ ፕሬዝዳትነትም ይወዳደራል።ፕሬዝዳት ዙማም እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ2014 በሚደረገዉ ምርጫ ይወዳደራሉ።ጉባኤዉ ሚሊየነሩን ነጋዴ ሲሪል ራማፎዛን ለፓርቲዉ ምክትል ፕሬዝዳትነት መርጧቸዋል።ሉድገር ሻዶምስኪ የዘገበዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።

ግዙፉ፥ የመቶ ዓመት አዛዉንቱ፥ የቀድሞዉ የጥቁሮች የነፃነት ተፋላሚዉ ፓርቲ ለሐምሳ-ሰወስተኛ ጠቅላላ ጉባኤዉ ከአራት ሺሕ በላይ አባላቱን ካንድ አዳራሽ አሳድሟል።«በ (ፓሪቲዉ) አመራርና» አሉ አንጋፋዉ ታጋይ ጄኮብ ዙማ ለጉባኤተኞቹ «በአባላት መካካል ያለዉን ልዩነት ማጥበብ አለብን» አከሉ።

ጉባኤዉን በጭፈራ-ፉከራ፥ በዘፈን- ዉዝዋዜ የጀመሩት ጉባኤተኞች የዙማን መልዕክት በጭብጨባ ፉጨት ተቀበሉት።ዙማ ላሉት ትልቅ ሐላፊነት ደግሞ ራሳቸዉ ዙማን በድጋሚ ሰየመ።ዙማ የተመረጡት በ2978 ድምፅ ነዉ።ብቸኛዉ ተቀናቃኛቸዉና ምክትልቻዉ ኽሌማ ሞትላንቴ ያገኙት ድምፅ 991 ድምፅ ነዉ።

ባለፉት ወራት በፓሪቲዉ መሪዎች መካካል ከፍተኛ ፍትጊያ ነበር።ዙማን ከሥልጣን ለማስወገድና ለመግደል ጭምር የተጠነሰ ሴራ ተጋልጧል።ዙማን በአስተዳደር ድክመት፥ በሴሰኝነት፥ በሙሰኝነት የሚወቅሱ የሚጠረጥሯቸዉም ብዙ ናቸዉ።ከፓርቲዉ ጠቅላላ ጉባኤ በፊት በተደረጉ አካባቢያዊ፥ ሙያዊና ፆታዊ ጉባኤዎች እንደተፀባረቀዉ ተቃዉሞ ወቀሳ-ትችቱ ሰዉዬዉ በተለይ በጠንካሮቹ የፓርቲዉ መዋቅራት በሴቶችና በወጣቶች ማሕበረት ዘንድ የነበራቸዉን ተቀባይነት አልሸረሸሩትም።

እና ሉድገር ሻዶምስኪ እንደሚለዉ ዙማ በድጋሚ መመረጣቸዉ ብዙም አላስገረመም።ያም ሆኖ የፀረ-ዘር መድሎዋ ነባር ታጋይ ሮሆዳ ካዳሊን የመሳሰሉ የፓርቲዉ አባላት ምርጫዉን፥ ከምርጫዉም በላይ የፓርቲዉን አመራር አሠራር የሚቀበሉት አይነት አይደለም።

«ከሁለት ሰይጣኖች አነስተኛዉን ሰይጣን የመምረጥ፥ ወይም ሁለት ትናንሽ ሰይጣኖችን የማወዳደር ጉዳይ አይደለም።በእኔ እምነት ኻሌማ ሞትላንቴም ሆኑ ዙማ-ሁለቱም ጥሩ አይደሉም»

አሉና ሮሆዳ-የፓርቲዉን የአባልነት ደብተር አሽቀጥረዉ ጣሉት።በጁሐንስበርግ ዩኒቨርስቲ የዲሞክራሲ ጥናት ተቋም ሐላፊ ስቴቫን ፍሪድማንም የደቡብ አፍሪቃዉያን የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት (ANC) በችግር መዘፈቁን ይመሰራሉ።

«አዎ፣-አሁን በብዙ ድምፅ የተመረጠ አመራር ተሰይሟል።የድርጅቱን መሠረታዊ ችግር ለመፍታት ግን የሚተክረዉ የለም።ዙማ ራሳቸዉ ባደረጉት ንግግር ችግሩ መኖሩን አምነዋል።እንዳለመታደል ሆኖ ግን መሪዎቹ ኤ.ኤን.ሲን ከችግር ከማዉጣት ይልቅ ችግር መኖሩን ማመኑን ብቻ መምረጣቸዉ ነዉ-አዛሳዛኙ።»


ዙማ ጉባኤዉን ሲከፍቱ ሕዝባቸዉንና ባለሐብቶችን ለማረጋጋት ሞክረዋል።ሐገራቸዉ አደጋ እንደማይገጥማት፥ ፓርቲያቸዉም የአፍሪቃን ምጣኔ ሐብት የምትመራዉን ሐገር መምራቱ እንደማይገደዉ አስታዉቀዉ ነበር።ተንታኞች ግን በዚሕ አይስማሙም።ከደቡብ አፍሪቃ ሕዝብ የሐምሳ-አራት ከመቶዉ የቀን ገቢ ከአንድ ዶላር ከሐምሳ ያነሰ ነዉ።በሐብታምና በዶሆች መካካል ያለዉ ልዩነት ያሁን ያክል ሰፍቶ አያዉቅም።

ከፖለቲካዉ ዓለም ርቀዉ የነበሩት ቱጃሩ ሲርየል ራማፎዛ የዙማ ምክትል ሆነዉ መመረጣቸዉ ስቴቫን ፍሪድማን እንደሚሉት ምጣኔ ሐብቱን ለማጠናከር መርዳቱ አይቀርም።

«በንግዱ ማሕበረሰብ ዘንድ ብዙ ይታመናሉ።በመካከለኛዉ መደብና በመገናኛ ዘዴዎች ዘንድም ዝነኛ ናቸዉ።በቅርቡ የሐገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳት እንደሚሆኑም አምናለሁ።ይሕ በመንግስቱ ዉስጥ አብይ ሚና እንዲኖራቸዉ ያደርጋል።በመሠረታዊዉ ጉዳይ ላይ ለዉጥ ማምጣቱን የሚያዉቅ ግን የለም።»

ራማፎዛ የዛሬ-ሃያ አምስት ዓመት ግድም የሠራተኛ ማሕበር መሪ በነበሩበት ወቅት ከሰወስት መቶ ሺሕ የሚበልጡ የማዕድን ሠራተኞች ማሳደም ችለዉ ነበር።በደቡብ አፍሪቃ ታሪክ ትልቁን አድማ የጠሩት ትልቅ ፖለቲከኛ ባለፈዉ ነሐሴ-የማዕድን ሠራተኞች ሲያድሙ የማዕድን ኢንዱስትሪ ተቆጣጣሪ ተቋም ተጠሪ ነበሩ።

በአድመኞቹና በፀጥታ አስከባሪዎች መካካል በተፈጠረዉ ግጭት በተገደሉት ሰላሳ-አራት ሠራተኞች ግድያ እጃቸዉ ሳይኖርበት አይቀርም ባዮች አሉ።ራማፎዛ ምርጥ የተባለዉ የደቡብ አፍሪቃን ሕገ-መንግሥት ያስረቀቁም ናቸዉ።አሁን ግን ቱጃር።በዚሕም ምክንያት ተቺዎቻቸዉ ሐብት ማጋበስን ሕዝብን ከመምራት ፖለቲከኝነት ጋር የመቀየጥ ተቃርኖ አብነት ያደርጓቸዋል።

የደቡብ አፍሪቃን ጉዳይ የሚያጠኑት ጀርማናዊዉ ተመራማሪ ሐይን ሙለር እንደሚሉት የዘር መድሎዉ ሥርዓት መወገድ እንደ ራማፎዛ አይነት ጥቂቶችን እንጂ አብዛኛዉን ደቡብ አፍሪቃዊ ብዙም አልጠቀመም።የአዲሶቹ መሪዎች ሐላፊነት ይሕን ልዩነት ማጥበብ ነዉ።

epa03510272 ANC Secretary General Gwede Mantashe (R) and NEC Member Jeff Radebe address the media conference on the outcome of the NEC meeting in Mangaung, South Africa, 15 December 2012, on the subject of court ruling. Members of the ANC in the North West took the party to court to prevent the province_s delegates from attending its 53rd national conference. The application was dismissed, but the court ordered the national conference to deal with the issue. At the previous ANC election, in 2007, incumbent President, Jacob Zuma ousted then-president Thabo Mbeki, creating rifts within the party. EPA/ELMOND-JIYANE/GCIS/HO
ጉባኤዉምስል picture-alliance/dpa
Delegates to the 53rd National Conference of the ruling African National Congress (ANC) sing and dance in the streets of Bloemfontein, December 15, 2012. The ANC starts its 5-day leadership election meeting on Sunday, which will likely see President Jacob Zuma re-elected for a second term. The ANC will also hammer out a final stance on issues such as mines nationalisation or taxation, and labour policy. REUTERS/Mike Hutchings (SOUTH AFRICA - Tags: POLITICS)
ጉባኤተኞች ሲደንሱምስል Reuters
[35746105] South Africa 53rd ANC National Conference epa03510886 South African President Jacob Zuma speaks during the 53rd ANC National Conference held in Mangaung, South Africa, 16 December 2012. The conference, held every five years, will decide the leader of the former struggle party. Jacob Zuma is facing a challenge to his leadership from deputy president Kgalema Motlanthe. EPA/KIM LUDBROOK +++(c) dpa - Bildfunk+++
ዙማ ተመረጡምስል picture-alliance/dpa

ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ