1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የመንገድ ሥራ መጓተት

ዓርብ፣ ጥር 1 2012

የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድር ርዕሠ ከተማ ሐዋሳን፣ ከዲላ፣ ከይርጋ ጨፌና ከሌሎች የሲዳማ ዞን እና የኦሮሚያ ከተሞች ጋር እንዲያገናኝ የታቀደ ነበር።አጠቃላይ መንገዱ ተሰርቶ ሳያበቃ፣ እስካሁን የተሰራዉ የአስፋልት መንገድ እየፈረሰ ነዉ

https://p.dw.com/p/3W0In
Äthiopien Stadtansicht Awassa
ምስል DW/S. Wegayehu

የመንገድ ስራ ተጓተተ

የተለያዩ የደቡብ ኢትዮጵያና የኦሮሚያ መስተዳድሮች ከተሞችን እንዲያገናኝ ታስቦ የዛሬ 6 ዓመት የተጀመረዉ የመንገድ ግንባታ እስካሁን አለመጠናቀቁን ነዋሪዎችና ሾፌሮች አስታወቁ።የዛሬ ሰባት ዓመት ግንባታዉ የተጀመረዉ መንገድ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድር ርዕሠ ከተማ ሐዋሳን፣ ከዲላ፣ ከይርጋ ጨፌና ከሌሎች የሲዳማ ዞን እና የኦሮሚያ ከተሞች ጋር እንዲያገናኝ የታቀደ ነበር።አጠቃላይ መንገዱ ተሰርቶ ሳያበቃ፣ እስካሁን የተሰራዉ የአስፋልት መንገድ እየፈረሰ ነዉ።የመንገዱን ሥራ በበላይነት የሚመራዉ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የደቡብ ጉዳይ የበላይ ኃላፊ ግን መንገዱ በሚቀጥሉት 4 ወራት ዉስጥ ይጠናቀቃል ባይ ናቸዉ።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ