1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዱባይ የ« ቡርጅ ኻሊፋ » ሕንጻ ምረቃ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 27 2002

ዱባይ በዓለም ውስጥ አሁን ክብረወሰን የያዘው 800 ሜትር ከፍታ ያለው «ቡርጅ ኻሊፋ» የተሰኘውን እጅግ ረጅሙ ህንጻ ትናንት በልዩ ሥነ ሥርዓት አስመረቀች።

https://p.dw.com/p/LLP0
የዱባዩ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃምስል picture-alliance/ dpa

በዓለም በተከሰተው የፊናንስ ቀውስ የተነሳ ከተመደበለት የጊዜ ሰሌዳ ከአንድ ዓመት በላይ ዘግይቶ ዘግይቶ ነው የተመረቀው። በዚሁ በአሜሪካው መሃንዲስ አድሪየን ስሚዝ በተቀየሰው እና በግንባታው ተግባር ላይ ብዙ የጀርመን ኩባንያዎች እና ጀርመናውያን የተሳተፉበት ታላቁ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ከስድስት ዓመት በፊት ግንባታው ሲጀመር «ቡርጅ ዱባይ» ወይም የዱባይ ጉልላት የሚል መጠሪያ ይዞ ነበር። ስሙ ለምን እንደተቀየረ እና ስለምረቃው ስነስርዓት የጄዳው ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

ነቢዩ ሲራክ/አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ