1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዳርፉር የሠላም ሥምምነት በቀጠር

ረቡዕ፣ የካቲት 11 2001

ሥምምነቱን ብዙዎች እንደ መልካም እርምጃ ቢያዩትም አንዳድ የዳርፉር አማፂ ሐይላት ግን አልተቀበሉትም

https://p.dw.com/p/Gwue
ዶክተር ኻሊል ኢብራሒም (ከግራ)የጅም መሪምስል AP

የሱዳን ማዕከላዊ መንግሥት እና የፍትሕና የእኩልነት ንቅናቄ በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ (JEM) የተሰኘዉ የዳርፉር ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሥለሠላም ለመደራደር ትናንት ተስማምተዋል።ዶሐ-ቀጠር ዉስጥ ሥለ ሰላም ድርድር የተደረገዉ ሥምምነት ስድስት አመት የዘለቀዉን የዳርፉርን የርስበርስ ጦርነት በሰላም ለመፍታት እንደመጀመሪያዉ እርምጃ ታይቷል።ሥምምነቱን ብዙዎች እንደ መልካም እርምጃ ቢያዩትም አንዳድ የዳርፉር አማፂ ሐይላት ግን አልተቀበሉትም።ጂም ከዳርፉር አማፂያን ሁሉ ትልቁ ነዉ።የጂዳዉ ዘጋቢያችን ነብዩ ሲራክ ዝርዝሩን ልኮልናል።