1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዳኛ ዉሳኔና የትራምፕ ይግባኝ በአሜሪካ   

ማክሰኞ፣ ጥር 30 2009

የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚበረክቱባቸዉ ሰባት ሃገራት ዜጎች ለጊዜዉ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ያሳለፉት ዉሳኔ በፍርድ ቤት ዉድቅ መደረጉ ለእነዚህ ሃገራት ዜጎች ለአሁኑ እፎይታ የፈጠረ መስሏል።

https://p.dw.com/p/2X7iS
USA Donald Trump besucht die MacDill Air Force Base in Tampa
ምስል Reuters/C. Barria

Beri. Washington DC (Trump's Appeal) - MP3-Stereo

 ሳንፍራንሲስኮ ግዛት በሚገኘዉ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር ዉሳኔዉን ለማስቀልበስ ያቀረበዉ አቤቱታ በድጋሚ በፌደራሉ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዉድቅ መደረጉ በሀገሪቱ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል። ጉዳዩ ወደ ሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተወሰደ ሲሆን ዛሬ ለአንድ ሰዓት የሚዘልቅ ክርክር እንደሚካሄድበት ይጠበቃል። የፕሬዝደንቱ ዉሳኔ ከሀገሪቱ ሕግ እንደሚፃረር የሚገልፁ ወገኖች ፍርድ ቤት የሀገሪቱን መሪ ዉሳኔ መጣል የቻለዉ የሕግ የበላይነት ያለባት በመሆኗ እንደሆነ ይናገራሉ። ከዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ