1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዳዳብ ስደተኞች መጠለያ ጣብያ

እሑድ፣ ሐምሌ 17 2003

በአፍሪቃው ቀንድ የተከሰተው የድርቅ አደጋ አስከፊነት ቀስ በቀስ ሀቀኛውን ገጽታውን እያሳየ ነው። በተመድ የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ዘገባ መሰረት፡ ግማሽ ሚልዮን ህጻናት በአሳሳቢ የረሀብ አደጋ የሚሞቱበት ስጋት ተደቅኖባቸዋል።

https://p.dw.com/p/RbrF
ዳዳብ መጠለያ ጣብያምስል Picture-Alliance/dpa

በኬንያ የሚገኘው የዳዳብ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በወቅቱ በሚያስተናግደው የስደተኞች ብዛት የተነሳ በዓለም ትልቁ የመጠለያ ጣቢያ ሆኖዋል። ሶስት መቶ ሰማንያ ሺህ ሰው ከሶማልያ፣ ከኢትዮጵያ እና ድርቅ ካጠቃቸው የኬንያ አካባቢዎች እየሸሹ ወደ መጠለያ ጣብያዉ ገብተዋል። የስደተኛው ቁጥርም ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ከመምጣቱም በላይ ማቆምያ የሚኖረዉ አይመስልም።

አንትየ ዲክሀንሰ

አርያም ተክሌ