1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ የሰላም ውል

ማክሰኞ፣ የካቲት 19 2005

11 የኮንጎ ጎረቤቶች በጋራ በኮንጎ ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት ፣ ለታጣቂ አማፅያንም ድጋፍ ላለመስጠት ቃል ገብተዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ ኮንጎ የሚገኘውን የድርጅቱን ሠላም አስከባሪ ኃይል ይዞታ ገምግሞ

https://p.dw.com/p/17lcm
ምስል Reuters

ሃገሪቱን በተሻለ ሁኔታ የሚረዳበትን መንገድ እንደሚፈልግ አስታውቋል ።

በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ግዛት ያለውን ግጭት ለማስቆም ይረዳል የተባለው የሰላም ውል ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ተፈርሟል ። ሃገሪቱን ለማረጋጋት በተመድ የተረቀቀውን ይህንኑ ውል የፈረሙት ኮንጎ ፣ ሩዋንዳ ፣ ብሩንዲ ፣ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ፣ አንጎላ ፣ ዩጋንዳ ደቡብ ሱዳን ፣ ደቡብ አፍሪቃ ፣ ታንዛንያ ፣ እና የኮንጎ ሪፐብሊክ ናቸው  ። የኮንጎ ጎረቤቶች በጋራ በኮንጎ ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት ፣ ለታጣቂ አማፅያንም ድጋፍ ላለመስጠት ቃል ገብተዋል ።  በፊርማው ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የተመድ ዋና ፀሃፊ ባን ኪሙን በአካባቢው ችግር ሲኖር ጣልቃ የሚገባ ብርጌድ ለማስፈር መታቀዱንም ተናግረዋል ። ውሉ ለሁለት አሠርተ-ዓመታት በእርስበርስ ጦርነት ተጠምዳ ለቆየችው አገር የአዲስ ዘመን ተሥፋን እንደፈጠረ ተገልጾዋል።   ስምምነቱ እንዲፈረም የሰላሙን ጥረት በዋነኛነት ያንቀሳቀሰው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሆኑ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። የዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ ኮንጎ ፕሬዚደንት ጆዜፍ ካቢላ በበኩላቸው አገራቸው ስምምነቱን ገቢር የማድረግ ግዴታዋን በአግባብ እንደምትወጣ ቃል ገብተዋል። በውሉ መሠረት የተቀሩት የጉባዔው ተሳታፊ ሃገራትም ወደፊት በጎረቤቲቷ አገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባትና ማንኛውንም የዓመጽ ቡድን ከመደገፍ መቆጠባቸው ግድ ነው።
 

Unterzeichnung Friedensabkommen im Kongo
ምስል Reuters

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ