1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሬስደኑ ዕልቂት ሲታወስ

ዓርብ፣ የካቲት 20 2001

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የተባበሩት ኃይሎች ባካሄዱት የቦምብ ድብደባ ከፍተኛ የህይወትና የንብረት ጥፋት ከደረሰባቸው የጀርመን ከተሞች ውስጥ ድሬስደን የተባለችው የምስራቅ ጀርመንዋ ከተመ ትገኝበታለች ።

https://p.dw.com/p/H2IM
ድሬስደን ከጦርነቱ በፊትና በኃላምስል AP

እ.አ.አ የካቲት አስራ ሶሶት ለየካቲት አስራ አራት አጥቢያ ይህች ከተማ በተደበደበች ወቅት በርካታ ህዝብ የተፈጀ ሲሆን ከተማይቱም እንዳልነበረች ሆናለች ። ድሬስደን በቦምብ የጋየችበት ይህ ለሊት በከተማይቱ ህዝብ ዘንድ በየዓመቱ ይታሰባል ። ይሁንና የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ በዚህ የመታሰቢያ ዕለት ወደ ከተማይቱ የሚመጡ ያልተጋበዙ ዕንግዶች የህዝቡን ስሜት እየረበሹ ነው ።