1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሬዝደኑ የፍርድ ቤት ዉስጥ ግድያ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 2 2001

እዚህ ጀርመን ድሴዝደን ከተማ ባለፈዉ ሳምንት ረቡዕ ያንዲት ግብፃዊት ነፍሰጡር እናት ፍርድ ቤት ዉስጥ በጩቤ ተወግቶ መሞት ከፍተኛ ቁጣና ቅሬታን አስነስቷል።

https://p.dw.com/p/IkYC
የተቃዉሞ ድምፅ በግብፅምስል picture alliance / dpa

የሟች ባለቤትም በጥይት መመታቱ ተዘግቧል። ከወራት በፊት በተመሳሳይ ፍርድ ቤት ዉስጥ አማቹን በጥይት ገድሎ ሌሎች ሁለት ሰዎች አቁስሏል። ዘገባዎች እንደሚሉት ወደፍርድ ቤት ሲገባ የመሳሪያ ፍተሻ አይደረግም። በግብፅ አሌክሳንደሪያ ስርዓተ ቀብሯ የተፈፀመዉ የሁለት ልጆች እናት የአሟሟት ሁኔታ በትዉልድ አገሯ ግብፅ ላስነሳዉ ቁጣ የጀርመን መንግስት የአገሪቱ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከግብፁ ፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባረክ ጋ በግንባር እንደሚነጋገሩበት ገልጿል።

ሸዋዬ ለገሠ/ነጋሽ መሐመድ