1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሬደዋ አመራር አካላት ግምገማ

ሐሙስ፣ መጋቢት 5 2011

በድሬደዋ አስተዳደር በቅርቡ ነዋሪው አደባባይ በመውጣት ያቀረበውን የአሠራር እና የመሪ ይለወጥልን ጥያቄ ምክንያት የፌደራል መንግሥት ተወካዮቹን ወደ አስተዳደሩ መላኩ ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/3F43a
Stadt Dire Dawa in Äthiopien
ምስል Hailegzi Mehari

«ለብልሹ አሠራሩ ተጠያቂዎች እንደሚኖሩ ተጠቁሟል»

በዚሁ መሠረትም የፖለቲካም ሆነ የፀጥታ መድፈረስ ችግሮችን ለይቶ የሚፈታና ዘላቂ መፍትሄ የሚሰጥ፤ እንዲሁም ለአመታት የቆዩና ልዩ ትኩረት የሚሹ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እልባት እንዲያገኙ የሚያስችሉ የማሻሻያ ሥራዎችን ሢሠራ ቆይቷል። የአሰስተዳደሩ ምክር ቤት ከትናንት በስትያ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ የዚሁ የማሻሻያው አካል ነው የተባለለትን ሹም ሽር አካሂዷል። በስብሰባው ላይ በቀረበ ሁለንተናዊ የግምገማ ዘገባም ከፍተኛ አመራሩ በከተማው ለሚታዩ በርካታ ችግሮች ተጠያቂ መሆኑን አመላክቷል። መሳይ ተክሉ ከድሬደዋ በጉዳዩ ላይ ዘገባ ልኮልናል።

መሳይ ተክሉ

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ